Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

Friday, 01 December 2017 01:39

ካንሰር

ሊያዘናጉን የማይገቡ 10 የካንሰር ምልክቶች

ብዙ ሃኪሞች ለካንሰር ህመም መጋለጥን ለሚያሳዩ ምልክቶች ትኩረት እንድናደርግ ሁሌም ይመክራሉ። በካንሰር ሙሉ በሙሉ ከመጠቃታችን አስቀድሞ ዶክተሮች ከደረሱበት ህመሙን መፈወስ ይቻላል። 

ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ነጥቦችን በፍፁም ቸል ልናላቸው እንደማይገባ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። በአለማችን ከ200 በላይ የካንሰር አይነቶች የሚገኙ ሲሆን፥ የተለመዱት የሳንባ፣ የጡት፣ የኩላሊት፣ የጉበት እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።

ቀጥሎ አስሩን የካንሰር የማስጠንቀቂያ ደወሎችን የዘረዘርንላችሁ ሲሆን ሁሉም ሰው ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ ሁላችንም አሁኑኑ ሼር እንድናደርገው ሳይቴክ ይጠይቃል።

1.  ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ

ብዙ ጊዜ ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ ዋነኛው የካንሰር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። 

ከ40 በመቶ በላይ የካንሰር ተጠቂዎች ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ ተጋላጭ እንደሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ በተለይም በሳንባና ጡት ካንሰር የተጠቁ ሰዎች ላይ ይታያል።

የክብደት መቀነስ የሚከሰተው ካንሰር ወደ ጉበታችን ሲስፋፋና የጉበትን ተግባር ሲያውክ ነው።

ስለሆነም ክብደት ለመቀነስ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረግን ካልሆነና ሆን ብለን ምግብ ካልቀነስን በስተቀር ተከታታይ የክብደት መቀነስ የካንሰር ህመም ምልክት ሊሆን እንደሚችል ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

2.  ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖችና ትኩሳት

ትኩሳት ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ሰውነታችን ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚያደርገውን ትግል ተከትሎ የሚከሰት ቢሆንም ለረዥም ጊዜ የቆየ ትኩሳት የካንሰር ምልክት ሳይሆን እንደማይቀር ይነገራል።

የደም ካንሰርም ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች፣ ትኩሳት፣ ድካም እና የመሳሳሉ ምልክቶችን ያሳያል።

3.  ድካም እና አቅም ማጣት

ከፍተኛ ድካምና የአቅም ማጣት በእንቅልፍና እረፍት የማይሻሻል ከሆነ ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል።

ይህ የድካም ስሜት ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል።

4. የትንፋሽ መቆራረጥ

ትንፋሽ ማጠር በተለያዩ አጋጥሚዎች የሚከሰት ቢሆንም የሳንባ ካንሰር ምልክት ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል።

በተለይም አየር ወደ ወጪ በምናስወጣበት ወቅት የፊሽካ ድምፅ የሚመስል ድምፅ የምናሰማ ከሆነ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት ተገቢ ነው ብለዋል ባለሙያዎቹ።

5. የማያቋርጥ ሳልና የደረት ህመም

ደረቅ ሳልና የጉሮሮ ቁስል የሳንባና ደም ካንሰር (ሉኪሚያ) ታማሚዎች ላይ በተደጋጋሚ ይከሰታሉ። ከዚህም በተጨማሪ ደረትን ሰቅዞ የመያዝ ስሜት ይሰማቸዋል።

ስለሆነም ተደጋጋሚ ደረቅ ሳልና የደረት ህመም ካስተዋሉ ሀኪሞን ያማክሩ።

ለስድስት ሳምንታት ያህል ከተለመደው ሁኔታ በተለየ የድምፅ መጎርነን በተለይም  በሚያጨሱ ሰዎች ላይ ከተከሰተ የሳንባ፣ የጉሮሮ እና መሰል ካንሰሮች መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።

6. የሆድ መነፋት

ያልተጠበቀና ሄድ መጣ የሚል የሆድ መነፋት ወይም መወጠር የካንሰር ምልክት ሳይሆን እንደማይቀር ነው የሚነገረው።

ከምግብ በኋላ ሆድ የመነፋትና የህመም ስሜትም የሆድ ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል። 

7.  ቃር

ቃር በሆድ ውስጥ የሚገኙ አሲዶች ወደ ጉሮሮአችን በሚመጡበት ጊዜ የሚከሰት የህመም ስሜት ሲሆን፥ ብዙ ጊዜ የተለመደ ነው።

ይሁን እንጂ ሁኔታው እየተደጋገመ ሲመጣ የጉሮሮ ካንሰር ምልክት ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች አረጋግጠዋል።

8.  የአንጀት ህመም

ያለምንም ምክንያት ለአራት ሳምንታት እና ከዚያም በላይ የዘለቀ የአንጀት ህመም በተለይም በአዋቂዎች ላይ ሲከሰት የአንጀት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

9. ምግብ የመዋጥ ችግር

ምግብ የመዋጥ ችግር ወይም ምግብ በጉሮሮና በደረት ላይ ተጣብቆ የቀረ የሚመስል ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከሄደ የጉሮሮ ወይም የሳንባ ካንሰር ምልክት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

ትኩስ ምግቦችን ለመውሰድ ያለመቻል እና ይህን ተከትሎ የሚመጡ የህመም ስሜቶችም ከላይ የጠቀስናቸው የካንሰር አይነቶች ምልክቶች መሆናቸው ተነግሯል።

ምግብ የመዋጥ ችግር የሳንባ ካንሰር ምልክትም ሊሆን እንደሚችል ነው የሚነገረው።

10. የቆዳና አይን ቀለም መቀየር

የቆዳ ቀለም ወደ ቢጫነት እንዲሁም የአይን ቀለም ነጭነት መቀየር ብዙ ጊዜ የጉበት እና የሀሞት ጠጠር ህመሞች ምልክቶች ሲሆኑ፥ በተመሳሳይ ለጉበትና የጣፊያ ካንሰር ምልክቶችም ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል። 

ይሀ ዕሁፍ የተገኘው ከፊስቡክ ንወ>>

የአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ደንብ

 

ይህ  ሁፍ የቀየ ቢሆንም ለግንዛቤ ይረዳልና አሰፈርነው / የሁፉን ባለቤት  በኢሜይል  -This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአዲስ አበባ ውስጥ ከሰሞኑ የመነጋገሪያ አጀንዳ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የነበረው አዲሱ የትራፊክ ደንብ  ነበር፡፡ ይህን ደንብ በተመለከተ ጥርት ያለ መረጃ ያለውም ሆነ መረጃ ሊሰጠኝ የሚችል ሰው ላገኝ አልቻልኩኝም ነበር፡፡ እንዲያውም ደንቡ የት እንደሚገኝ ጥያቄውን ያቀረብኩላቸው የትራፊክ ፖሊሶች የት እንደሚገኝ እንኳ ደንቡ የሚገኝበትን ቦታ አያውቁም ነበር፡፡ ኋላም ይህን ያውቃሉ ብዬ የገመትኳቸውን ኢትዮጵያዊ ጠበቆች የጠየቅኩኝ ቢሆንም እነርሱም ደንቡ የሚገኝበትን ቦታ አያውቁም ነበር፡፡ በደፈናው ግን አብዛኛው አዋጅ ወደሚገኝበት የብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት ይጠቁሙኝ ነበር፡፡ ይህን ደንብ ኢትዮጵያዊ ጠበቃ፣ ኢትዮጵያዊ ትራፊክ ፖሊስ ካላወቀው ማን ሊያውቀው ይችላል በማለት ተገረምኩኝ፡፡ የኋላ የኋላ የዛሬ ሳምንት ደንቡ የወጣው በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሲሆን የሚገኘውም በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብቻ እንደሆነ ለመገንዘብ ችያለሁኝ፡፡

እስኪ ከራሱ ከአዋጁ እንጀምር፡፡ የአዋጁ መግቢያ እንደሚለው ይህ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ደንብ ሊወጣ የቻለው በከተማችን ውስጥ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሠው ሕይወትና ንብረት እንዲሁም በመስተዳዳሩ ኢኮኖሚ ላይ የሚደርሠው ጉዳት በየዕለቱ ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ እንዲያዉም አሣሣቢ ደረጃ ላይ በመድረሡ ምክንያት እንዲሁም ከዚህም በተጨማሪ እያደገ ከመጣው የአለም ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ በአሽከርካሪዎች ምክንያት ለአደጋ የሚያጋልጡ ሀኔታዎችን ለመቆጣጣር የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር በማስፈለጉ ምክንያትና ከዚህ ቀደም በነበሩ የትራፊክ ደህንነት ደንቦች ውስጥ ያልተካተቱና አዳዲስ የጥፋት አይነቶች እየተከሠቱ በመምጣታቸዉ የተነሳ አሁን ካለንበት የእድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣም ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓትን የተከተለ ደንብ በማሥፈለጉ እንደሆነ ምክንያት ይህ የትራፊክ ደንብ ቁጥር 27/2ዐዐ2 ሊወጣ ችሏል፡፡

ስለ ትራፊክ ደንቡ አላማ ይሄንን ያህል ካልን ቀጥሎ የሚነሣው ጥያቄ ይህ ደንብ ተፈፃሚነቱ እስከ የት ድረስ ነው የሚለው ሲሆን የዚሁ የትራፊክ ደንብ አንቀፅ 3 እንደሚደነግገው ተፈፅሚነቱ በአዲስ አበባ ከተማ ክልል ውስጥ ብቻ ሆኖ በማናቸውም የትራፊክ አንቅስቃሴ ባለበት ቦታ ወይም የማቆሚያ ስፍራ ላይ ሁሉ ነው፡፡

የጥፋት አይነቶችና የቅጣት አወሣሠን

አንቀፅ 4 ስለጥፋትና የቅጣት አወሣሠን ይዘረዝራል፡፡ በዚህም መሠረት አንድ አግረኛ 1956 . የወጣውን የትራንስፓርት ማሻሻያ ደንብ በአንቀፅ 61-65 ላይ የተደነገጉትን ጥሶ ከተገኘ ለሚደርስበት አደጋ ለጥፋቱ አንዳደረገው አስተዋፅኦ መጠን በሙሉ ወይም በከፊል ሀላፊ ይሆናል፡፡ ክልከላው በመጣሱም 1996 . በወጣው የወንጀል ህግ መሠረት ይቀጣል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉዳት ያደረሰው አሽከርካሪ 1956 . በወጣው የትራንስፖርት ማሻሻያ ደንብ አንቀፅ 83(2)(3) የተጠቀሱትን ግዴታዎች መፈፀም አለበት፡፡

የመጀመሪያ ቅጣት እርከን

አንቀፅ 4(3) ከመጀመሪያ እርከን - ሠባተኛ እርከን ድረስ የሚቀመጡ ጥፋቶች የሚያስቀጡትን የቅጣት መጠን /ብር/ ይደነግጋል፡፡ ከዚሁ ደንብ ጋር የተያያዘው ሠንጠረዝ ደግሞ የጥፋቶቹን አይነት ይዘረዝራል:: በዚህም መሠረት ቀጥሎ የተዘረዘሩት ጥፋቶች በደንቡ መሠረት የመጀመሪያ እርከን ጥፋቶች ሲሆኑ የቅጣት መጠናቸውም 6 ብር ነው፡፡

1.       ተሽከረካሪን ያለአግባብ የጎተተ

2.       መንገድ ላይ እንሰሳትን የነዳ

3.       የተሟላ የጭነት ማቀፊያ /ስፓንዳ/ የሌለው ተሽከርካሪ

4.       የጥሩንባ ድምፅ ያለአግባብ (በማይገባ ቦታ) የተጠቀመ

5.       በትርፍ ጭነት ላይ ምልክት ያላደረግ

6.       ከፍተኛ ጭስ የሚያጨስ ተሽከርካሪ የነዳ

7.       የለማጀ ምልክት ሣይለጥፍ እና ባልተወሠነ ቦታ እንዲሁም ሠአት ተሽከርካሪ መንዳት ያስተማረ

8.       ለሀዘን ከሆነ ሣያሰፈቅድ ወይም ተክሎ ወዲያው በአቅራቢያው ላለው የፖሊስ ጣቢያ ሣያሳውቅ ድንኳን በመንገድ ላይ ያቆመ

9.       መንገድ ላይ ተሽከርካሪ ያሣጠበ

10.   ለእግረኛ ክልክል በሆነ መንገድ ላይ ያቋርጠ

11.   ለማቋረጥ ከተፈቀደለት ዉጪ በቀለበት መንገድ ላይ ያቋርጠ

12.   ለእግረኛ ከተዘጋጀ መንገድ ዉጪ በተሽከርካሪ መንገደ ላይ የተጓዘ

13.   በመንገድ ላይ የንግድ ሥራ የሰራ

14.   የመጀመሪያ ሕክምና ኪት በተሽከርካሪው ያልያዘ

15.   ውሀ በእግረኛ ላይ የረጨ

16.   በብልሽት/ በግጭት ምክንያት መንገድ ላይ የወደቁ የተሽከርካሪ ስብርባሪዎችን ያላፀዳ

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ጥፋቶች ህጉ የመጀመሪያ እርክን ጥፋቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ሲሆኑ ማንኛውም አሽከርካሪ ሆነ እግረኛ እንዚህን ጥፋቶች አጥፍቶ ቢገኝ 6 ብር ቅጣት የሚቀጣ ይሆናል፡፡

የሁለተኛ ቅጣት እርከን

የሚከተሉት የጥፋት አይነቶች የሁለተኛ ቅጣት እርከን ላይ የሚቀመጡ ጥፋቶች ሲሆኑ ማንኛውም አሽከርከሪ ሆነ እግረኛ እንዚህን ጥፋቶች አጥፍቶ የተገኝ እንደሆነ 8 ብር የሚቀጣ ይሆናል ፡፡ ጥፋቶቹም

1.       ወደማይሄድበት አቅጣጫ ምልክት ያሳየ

2.       ምልክት ሣያሳይ ተሽከርካሪ ካቆመበት ቦታ ያንቀሣቀሠ ወይም ያቆመ

3.       በተሽከርካሪ የወጪ አካል ላይ ሠው የጫነ

4.       የቀስት አቅጣጫ የለቀቀ

5.       የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ የነዳ

6.       ያለአግባብ ወደ ኋላ ያሽከረከረ

7.       ለአላፊ ተሽከርካሪ ቅድሚያ የከለከለ

8.       በተከለከለ ቦታ በትራፊክ ደሴት እንዲሁም በድልድይ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

9.       በትራፊክ ምልክት መብራት አጠገብ ተሽከርካሪ ያቆመ

10.   በባቡር ሀዲድ አጠገብ ተገቢውን ጥንቃቄ ያላደረገ

11.   መብራት እያለው በማብሪያ ጊዜ ሣያበራ ያሽከረከረ

12.   የመንጃ ፍቃድ /የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ሳይዝ ያሽከረከረ፣ ያላሳደሰ

13.   ያለፈቃድ ተሽከርካሪ መንዳት ያሰተማረ

14.   ሠሌዳው የተደመሠሠ ወይም የተቆረጠ ወይም የተሸፈነ ተሽከርካሪ ያሽከረከረ

15.   ከተፈቀደው ፍጥነት በታች ያሽከረከረ

16.   በእጅ የሚገፋ ወይም የሚሣብ ጋሪ በዋና መንገድ ላይ የገፋ ወይም የሳበ

17.   የጉዞ መስመር ጠብቆ ያላሽከረከረ

Zስተኛ የቅጣት እርከን

የጥፋት አይነቶች

1.       25 ሜትር ርቀት ምልክት ሳያሣይ የተሽከርካሪውን አቅጣጫ የቀየረ

2.       የሚከለከል ምልክት የጣሠ

3.       የሚያስገድድ ምልክት የጣሠ

4.       ደሴት በግራ ያቋርጠ

5.       በጠባብ መንገድ ላይ ያቆመ

6.       በመታጠፊያ መንገድ ላይ ያቆመ

7.       የመንገድ አከፋፋይ ደሴት/መስመር ያቋርጠ

8.       የጭንቅላት መከላከያ /ሄልሜት/ ሣያደርግ ሞተር ሣይክል ያሽከረከረ ወይም ከኋላ ሠው ያፈናጠጠ

9.       የተበላሸ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ የጠገነ

10.   ከተወሠነለት መቀመጫ ወይም የጭነት ልክ በላይ የጫነ

11.   በአሽከርካሪው ላይ የተጫነውን ጭነት በሚገባ ያላሠረ ወይም ያላለበሠ

12.   ሳያስፈቅድ እይታን የሚከለክሉ መጋረጃዎችን ወይም ተለጣፊ ላስቲክ የለጠፈ

13.   አፈር፣ አሸዋ፣ ድንጋይና የመሳሰሉትን ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ያራገፈ ወይም እንዲራገፍ ያደረገ

14.   ሌሎች የትራፊክ ፍሰትን የሚያሠናክሉ ድርጊቶችን የፈፀመ

15.   በተሽከርካሪው ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ

16.   የተለጣፊ ምልክት /ቦሎ/ ያልለጠፋ

17.   የአሽከርካሪን እይታ የሚከለክል ማንኛውም አይነት ማስታወቂያ ወይም ሌላ ነገር መንገድ ዳር ወይም መሀል ላይ የተከለ ወይም የገነባ

18.   ለተለያዩ ተግባራት መንገደ ቆፍሮ ወደነበረበት ሳይመልስ የቀረ

 

እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው የጥፋት አይነቶች ህጉ 3 እርከን ላይ ያስቀመጣቸዉ ሲሆኑ ማንኛዉም አሽከርካሪም ሆነ ግለሰብ ጥፋቱን ፈፅሞ የተገኝ እንደሆነ በትራፊክ ደንቡ አንቀፅ 4/3// መሠረት 1ዐዐ ብር ይቀጣል፡

አራተኛ የቅጣት እርከን

እነዚህ የቅጣት አይነቶች የትራፊክ ደንቡ በአራተኛ የቅጣት አርከን ላይ ያሰቀመጣቸው እያንዳንዳችው 12 ብር ቅጣት የሚያስቀጡ ናቸው፡፡

1.       ተሽከርካሪ በአንቅስቃሴ ላይ እያለ ተሣፋሪ የጫነ ወይም ያወረደ

2.       በተሽከርካሪ መግቢያ ወይም መዉጫ በር ላይ የቆመ

3.       አመታዊ የተሽከርካሪ ደህንነት ምርመራ ያላደረገ

4.       ግልፅ ጉድለት ያለው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ

5.       በትራፊክ ደሴት ላይ ያሽከረከረ

6.       ከተማ ውስጥ ከባድ መብራት /ባውዛ/ የተጠቀመ

7.       ያለማንፀባረቂያ ምልክት የተበላሸ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ያቆመ

8.       2 ሠአት በላይ ከባድ ተሽከርካሪ በመንገደ ላይ ያቆመ

9.       በሠንሠለት የሚሽከረከርና በሠአት 1 . በታች የሚጓዝ ልዩ ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ያሽከረከረ

10.   በአውቶቢስ መቆሚያ ስፍራ ላይ ሌላ ተሽከርካሪ ያቆመ

11.   ከባድ ተሽከርካሪ ላይ ከኃላ አንፀባራቂ ምልክት ሣይለጥፍ ያሽከረከረ

አምስተኛው የቅጣት እርከን

ከዚህ በታች የተቀመጡት ጥፋቶች የትራፈክ ደንቡ አንቀፅ 4/3// ላይ አምስተኛ እርከን የጥፋት አይነቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ሲሆኑ እያንዳንዳቸው ጥፋቶች 14 ብር መቀጫን ያስከትላሉ ጥፋቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.       ደረጃውን ባልጠበቀ መንጃ ፈቃድ /የአሽከርከሪነት ብቃት ማረጋገጫ ያሽከረከረ

2.       መስቀለኛ መንገድ ላይ ቅድሚያ ያልሠጠ

3.       ቅደሚያ መሠጠት ሲገባው የከለከለ

4.       የትራፈክ መብራት ወደቀኝ መታጠፍ ለሚፈቅድለት ተሽከርካሪ መንገድ የዘጋ

5.       አለአግባብ ተሽከርካሪ የቀደመ

6.       የተሽከርካሪ በር ከፍቶ ያሽከረከረ

7.       በህግ ከተወሰነው ከፍታ ርዝመት ወይም ስፋት ውጭ ጭነት የጫነ

8.       የእግረኛ መንገድ ለተለየ አገልግሎት ያዋለ

9.       ከሀዘን በስተቀር ያለፓሊስ ፈቃድ በመንገድ ላይ ድንኳን የተከለ

10.   የፓሊስ ወይም በጎ ፈቃደኛ ትዕዛዝ ያልፈፀመ

11.   ዕደሜያቸው ከሠባት አመተ በታች የሆኑ ህፃናት በተሽከርካሪ ጋቢና አሣፍሮ ያሽከረከረ

12.   ህጋዊ ስልጣን ካለው አካል ፈቃድ ሣያገኝ በመንገድ ትራፊክ ምልክት የተጠቀመ

ስድስተኛ የቅጣት እርከን

እዚህኛው እርከን ላይ የሚቀመጡት ጥፋቶች ህጉ ከባድ ብሎ ያስቀመጣቸው የትራፊክ ደንብ የጥፋት አይነቶች ሲሆኑ እያንዳንዳቸውም 16 ብር ቅጣት ያስከትላሉ፡፡ ጥፋቶቹም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

1.       ሠክሮ አደንዛዥ ዕፅ ወይም ጫት ውሰዶ ወይም ሺሻ አጭሶ ያሽከረከረ

2.       የጆሮ ማዳመጫ /ኤር ፎን/ ጆሮው ውስጥ በመክተት ሬድዮ እያዳመጠ ወይም ሞባይል እያናገረ ያሽከረከረ

3.       ሞባይል ስልክ በእጁ ይዞ ወይም Dከርካሪው ላይ ገጥሞ እያናገረ ማንኛውንም አይነት ተሽከርካሪ ያሽከረከረ

4.       የተሽከርካሪ የመቀመጫ ቀበቶ ሣያስር ወይም ሌሎች እንዲያስሩ ሣያደረግ ያሽከረከረ

5.       ሬዴዮ፣ ቴኘ ሲዲ በከፍተኛ ደምፅ ከፍቶ እያዳመጠ ያሽከረከረ

6.       የመንጃ ፈቃድ / የአሽከረካሪ ብቃት ማረጋገጫ ሳይኖረዉ ያሽከረከረ

7.       የመንጃ ፈቃድ/ የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ለሌለዉ ሰዉ እንዲያሽከረክር የሰጠ

8.       ለእግረኛ ቅድሚያ ያልሰጠ

9.       ቀይ የትራፊክ መብራት የጣሰ

10.   በህግ ከተወሠነው ፍጥነት በላይ ያሸከረከረ

11.   የእሳት አደጋ ተሽከርካሪ ዉሀ መሙያ ቦታ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

12.   ለአደጋ አገልግሎት ተሽከርካሪ ቅድሚያ ያልሰጠ

13.   በእሳት አደጋ ወይም ሆስፒታል በር ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

14.   በእግረኛ መንገድ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

15.   በእግረኛ ማቋረጫ ላይ ተሽከርካሪ ያቆመ

16.   ምንም መብራት ሣይኖረው ያሽከረከረ

17.   በተከለከለ መንገድ ወይም አቅጣጫ  ያሽከረከረ

18.   መሀል መንገደ ላይ ተሳፋሪ ወይም ጭነት የጫነ ወይም ያወረደ

19.   የትራፊክ አደጋ ፈፅሞ ቦታው ላይ ያልቆመ

20.   ቴሌቪዥን ወይም ቪዲዩ ተሽከርካሪ ውስጥ እያየ ያሽከረከረ

21.   በትራፊክ መብራት ላይ ወይም በመሰቀለኛ መንገድ ላይ ወይም ሌላ ማናቸውም መንገድ ላይ በልመና ላይ ለተሠማሩ ሠዎች ገንዘብ ያሠጠ ወይም የሠጠ ወይም ማንኛውንም አይነት ግብይት ያረገ ወይም ያሰደረገ

22.   የመንገድ ትራፊክ ምልክት ያበላሸ የሚያስተላልፈውን ይዘት የቀየረ ወይም ከተተከለበተ ቦታ ያዞረ ወይም በመንገድ ምልክት ላይ ማስታወቂያ የለጠፈ

23.   ተሽከርካሪው ከተፈቀደለት አገልግሎት ውጪ ለሌላ አገልግሎት የተጠቀመ

ሠባተኛ የቅጣት እርከን

በትራፊክ ደንቡ አንቀፅ 4/3//በሠባተኛ የቅጣት እርከን ላይ የተቀመጡት የጥፋት አይነቶች ህጉ በተለየ ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ የትራፊክ ደንብ ጥፋት ብሎ ያስቀመጣቸው ሲሆኑ የቅጣት መጠናችውም 3ዐዐ.ዐዐ ብር ጀምሮ እንደየጥፋቱ አይነት አስከ ብር 7ዐዐ.ዐዐ የሚያስቀጡ ጥፋቶች ናችዉ፡፡ እነሡም በብር 3ዐዐ.ዐዐ የሚያስቀጡ ጥፋቶች

1.       በቂ ርቀት ሣይጠብቅ በማሽከርክር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

2.       ያለአግባብ ተሽከርካሪን ወደ ኋላ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ በብር 350.00 የሚያስቀጡ ጥፋቶች

3.       ማንኛዉም አሽከርካሪ ተሽከርካሪን ካቆመበት ያለጥንቃቄ ሲያነሣ፣ ተሽከርካሪን ደርቦ ሲታጠፍ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነና እንዲሁም ተሽከርካሪን በመገልበጥ በራሱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ለዚሁ ጥፋት ብር 35.ዐዐ ቅጣት የሚቀጣ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ህጉ 4ዐዐ.ዐዐ ብር የሚያስቀጡ ጥፋቶች ብሎ የዘረዘራቸዉ የጥፋት አይነቶች አሉ፡፡ እነሱም

1.       የተሽከርካሪ መሪ ያለአግባብ ተጠቀሞ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

2.       ከመጋቢ መንገድ አቅጣጫ Dከርካሪ እያሽከረከረ ወጥቶ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

3.       ተሽከርካሪን እያሽከረከረ ከመንገድ ወጥቶ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

4.       ለሌላ ተሽከርካሪ በተገቢዉ ቦታ ላይ ቅድሚያ በመከልከል በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

5.       ተሽከርካሪ እያሽከረከረ በቀኝ በኩል በመቅደም በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

6.       ያለደረጃ የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ይዞ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

7.       የአደጋ ተካፋይ ሆኖ ያመለጠ ወይም ወደሚመለከተው አካል ያልቀረበ ናቸዉ፡፡

ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ደግሞ ህጉ 5ዐዐ.ዐዐ ብር ቅጣት ያስከትላሉ ብሎ ያስቀመጣችው የጥፋት አይነቶች ሲሆኑ ማንኛውም ሠው እነዚህን ጥፋቶች አጥፍቶ የተገኘ እንደሆነ 5ዐዐ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል የጥፋቶቹም አይነት

1.       ከተፈቀደለት ፍጥነት በላይ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

2.       የሚያስገድድ፣ የሚያስጠነቅቅ የሚከለክል ወይም ሌላ በመንገድ ላይ የሰፈረ የትራፊክ ምልክት ወይም ማመልከቻ በመጣስ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

3.       በህግ ከተፈቀደው ከፍታ፣ ርዝመት፣ ወይም ስፋት በላይ ተሽከርካሪው ላይ ጭኖ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

4.       ግራ መንገድ ውስጥ ገብቶ እያሽከረከረ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

5.       አደንዛዥ ዕፅ ወይም መጠጥ ጠጥቶ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

6.       የቴክኒክ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ፡፡

በመጨረሻ የምናገናቸው ሠባተኛ የቅጣት እርከን ላይ የተቀመጡትን የጥፋት አይነቶች ሲሆን ማንኛውም ሠው እነዚህን አይነት ጥፋቶች አጥፍቶ ቢገኝ 7ዐዐ.0 ብር ቅጣት ይከፍላል፡፡ ጥፋቶቹም እንደሚከተሉት ትዝርዝረዋል፡፡

1.       የቴክኒክ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ የትራፊክ ምልክትና ማመልከቻ ጥሶ በማሽከርከር በንብርት ላይ ጉዳት ያደረሠ

2.       የቴክኒክ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ እጽ ሰክሮ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ

3.       መንጃ ፈቃድ ሣይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብርት ላይ ጉዳት ያደረሰ

4.       ተሽከርካሪ እያሽከረከረ በንብረትም ሆነ በሠው ላይ አደጋ አድርሶ ያመለጠ

5.       ለአምቡላንስ ወይም ለእሣት አደጋ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ከልክሎ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሠ

እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው ከባድ ጥፋቶችን አጥፍቶ የተገኘ ማንኛውም ሠው በደንቡ መሠረት ተገቢውን የቅጣት ክፍያ ማለትም 7ዐዐ.ዐዐ ብር ይከፍላል፡፡

የትራፊክ ደንብ አንቀፅ 4/4/ እንደሚደነግገው ከሆነ ማንኛውም አሽከርካሪ በተደጋጋሚ ጥፋት ከፈፀመ ከላይ ከዘረዘርናቸው የገንዘብ ቅጣቶች በተጨማሪ የመንገድ ስነ ሥርአት ፈተና ወይም የመሰናክል ፈተና ወይም የከተማ ዉስጥ ማሽከርከር ፈተና በድጋሚ እንዲወስድ በማድረግ ወይም ለተለያየ ጊዜ የሚቆይ የመንጃ ፈቃድ/የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ዕገዳ በማድረግ ወይም የመንጃ ፈቃዱን/የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ለዕድሜ ልክ በመንጠቅ ይቀጣል፡፡ የቅጣቱ አፈፃፀምም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

የግል ተሽከርካሪ አሽከርካሪ

ከሁለት ጊዜ በላይ ከባድ ወይም እጅግ ከባድ የትራፊክ ደንብ ጥፋት የፈፀመ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ የመንጃ ፈቃዱ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ተይዞ

1.       Zስተኛ የጥፋት ሪኮርድ 3 ወር ተሽከርካሪ እንዳያሽከረክር ይታገዳል

2.       ለአራተኛ የጥፋት ሪኮርድ 6 ወር ተሽከርካሪ እንዳያሽከረክር ይታገዳል

3.       ለአምስተኛ ጊዜ የጥፋት ሪኮርድ 1 አመት ተሽከርካሪ እንዳያሽከረክር ይታገዳል

4.       ለስድስተኛ ጊዜ የጥፋት ሪኮርድ 2 አመት ተሽከርካሪ እንዳያሽከረክር ይታገዳል

5.       ለሠባተኛ ጊዜ የጥፋት ሪኮርድ የመንጃ ፈቃድ/ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ውድቅ ይሆናል፡፡ ሆኖም 3 አመት በኃላ አዲስ መንጃ ፈቃድ ሊያወጣ ይችላል፡፡

ከአምስቴ በላይ ማንኛውንም የትራፊክ ደንብ ጥፋት የፈፀመ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ የመንጃ ፈቃዱ ወይም የአሽከርካሪ ብቅት ማረጋገጫ ፈቃዱ ተይዞ

1.       ለስድስተኛ ጥፋት ረኮርድ የመንገድ ሥነ-ስርዓት ፈተና በድጋሚ እንዲውስድ ይደረጋል

2.       ለሠባተኛው ጥፋት ሪኮርድ የመሠናክል ፈተና በድጋሚ እንዲወስድ ይደረጋል

3.       ለስምንተኛ የጥፋት ሪኮርድ የከተማ ውስጥ ማሽከርከር ፈተና በድጋሚ እንዲወስድ ይደረጋል

4.       ለዘጠነኛ የጥፋት ሪኮርድ መንጃ ፈቃድ / የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ውድቅ ይሆናል፡፡ሆኖም 6 ወር በኃላ አዲስ መንጃ ፈቃድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሊያወጣ ይችላል፡፡

የሌላ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ

Zስት ጊዜ በላይ ከባድ ወይም እጅግ ከባድ የትራፊክ ደንብ ጥፋት የፈፀመ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ የመንጃ ፈቃዱ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ተይዞ እንደየጥፋት ሪኮርድ 6 ወር ጀምሮ እስክ ሁለት /2/ አመት ድረስ ተሽከርካሪ እንዳያሽከረክር ይደረጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሠባተኛ የጥፋት ሪኮርድ መንጃ ፈቃድ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ዉድቅ ይሆናል፡፡ሆኖም ከአምስት አመት በኋላ አዲስ መንጃ ፍቃድ/የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ሊያወጣ ይችላል፡፡ይኸው አሽከርካሪ ለስምንተኛ ጊዜ ሪኮርድ ከተያዘበት የመንጃ ፈቃዱ/ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡

ከሠባት ጊዜ በላይ ማንኛውም የትራፊክ ደንብ ጥፋት የፈፀመ ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ የመንጃ ፈቃድ ተይዞ

1.       ለስምንተኛ የጥፋት ሪኮርድ በድጋሚ የመንገድ ስነስርአት ፈተና  እንዲወስድ ይደረጋል

2.       ለዘጠነኛ የጥፋት ሪኮርድ የመሠናክል ፈተና በድጋሚ እንዲወስደ ይደረጋል

3.       ለአስረኛ የጥፋት ሪኮርድ የከተማ ውስጥ ማሽከርከር ፈተና በድጋሚ እንዲወስድ ይደረጋል፡፡

 

4.       ለአስራአንደኛ የጥፋት ሪኮረድ የመንጃ ፍቃድ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ውድቅ ይሆናል፡፡ ሆኖም 1 አመት በኃላ አዲስ መንጃ ፈቃድ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሊያወጣ ይችላል፡፡

 

የትራፊክ ደኅንነት ጉዳያችን አድሮ ቃሪያ ከርሞ ጥጃ ለምን ሆነ? . . . 7 ወሳኝ ነጥቦች

Posted on May 30, 2013by Dawit Worku

 ዳዊት ወርቁ

ግንቦት 2005

እንደ የዓለም ጤና ተቋም (WHO) ወቅታዊ መረጃ ከሆነ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ ብቻ የተቀጠፈው ነፍስ ቁጥር

22,786 ደርሷል፡፡  ይህም ማለት በተለያዩ ምክንያት ከሚከሰተው ሞት ከመቶ 2.77% ሲሆን፣ አማካይ የሟቾቹ ዕድሜ 37.83 ነው፡፡ ሀገሪቱ በትራፊክ አደጋ ብዛትም ከዓለም 12 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ (በነገራችን ላይ በድህነትም 12 ደረጃ ላይ ናት)

እንደ  ኦል አፍሪካን ዶትኮም ድረ ገጽ ከሆነ፣ በሀገራችን በየዓመቱ 2000 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ 4-5 ሚሊየን ብር የሚሆን ጥፋትም በንብረትና ቁስ  ላይ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ 10 ተሽከርካሪዎች 160  ሰዎች ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት፣ ባደጉት አገሮች ግን 2 እና 3 ሰው ብቻ ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በዋነኝነት የትራፊክ አደጋ የሚከሰው

1.       በአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ (Inefficient of drivers)

2.      የሌሊት ጉዞ (Night Travel)

3.      ጫት ቅሞና አልኮል ጠጥቶ በማሽከርከር (deriving Under the Influence of Khat & Alcohol)

4.      ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር (Over Speeding)

5.       ደህንነታቸው አስጊ ደረጃ ላይ በደረሱ ተሽከርካሪዎች በመገልገል (Poor vehicle technical fitness) ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡

ሚዲያዎች ሁሉ፣ በተለይም FM ራዲዮኖቻችን ቢያንስ በቀን ለአንድ ጊዜ ያህል  በመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ዙሪያ አንዳች ነገር ሳይሉ ውለው አድረው አያውቁም፡፡ ይሁንና፣ ጉዳዩ ባለበት ቦታ እየረገጠ ይመስላል፡፡ ፈቅ የሚል ነገር ጨርሶ አይታይም፡፡ ሁሉ ውይይት፣ ሁሉ ልፈፋ፣ ሁሉ የትምህርት ጋጋታ ውኃ እየበላው ይመስላል፡፡ በመንገድ ትራፊክ አደጋ የሚጎዳውም ሰው ከዕለት ዕለት እየጨመረ ነው፡፡

ለመሆኑ ለምንድነው በትራፊክ ጉዳያችን ላይ ሥር ነቀል የሆነ ለውጥ ማምጣት ያልታቻለውና አደጋውን መቀነስ ያልተቻለው? . . . ዕነሆ ሰባት ወሳኝ ነጥቦች፣

1.  የአንድ ሰሞን ርብርብ

በትራፊክ ጉዳዮቻችን ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት ያልተቻለው አደጋውም ከዕለት ወደዕለት እየከፋና እያደገ የሄደበት የመጀመሪያው ምክንያት፣ ምንም እንኳ ህግ አውጪዎቹና አጽዳቂዎቹ ተስማምተው፣ አሜን ብለው ህግና ደንቡን ቢቀርጹም፣ ማስተግበሩና አስተግባሪዎቹ ግንጉድ አንድ ሰሞን ነውእንዲሉ፣ የአንድ ሰሞን ጉዳይ በመሆናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ያለዜብራማቋረጫ ያቋረጠ እግረኛ እንዲህና እንዲያ ይደርጋል፣ ይባልና ለአንድ ሰሞን ምድረ ትራፊክ ፖሊስ ተብዬ ሁላ በዘመቻ ታጥቆ ይነሳል፣ ከዚያም ለጥቂት ቀናት ወጧ እንዳማረላት ባልቴት ጉድጉድ ካሉ በኋላ ሁሉንም ነገር እንዳለፈ ውኃ ይረሱታል፡፡

ትርፍ መጫን ከዚህ በኋላ በፍጹም አይፈቀድምበተባለ ማግሥት፣ ትርፍ ሰው ሳይሆን ችቦ የጫኑ የሚመስሉ ሃይገሮችና ተሳፋሪውን እንደአሻንጉሊት የሚቆጥሩት የአዲስ አበባ ሚኒባስ ታክሲ፣ ሾፌሮች ለቀናት ያህል ከትራፊክ ፖሊሶች ጋር የአይጥና ድመት እንካ ሰላንቲያቸውን ከተጫወቱ በኋላ፣ ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞው ፍሰቱ ይቀጥላል፡፡

የመኪኖች አካላት ደኅንነት ሁናቴ፣ የመንጃ ፈቃድ ትክክለኛነት፣ የአሽከርካሪ ብቃት፣ ቀበቶ፣ ወዘተ . . . ለአንድ ሰሞን ክትትል ከተደረገባቸው በኋላ ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞው ልምምድ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ የትራፊክ ደኅንነታችን አድሮ ቃሪያ፣ ከርሞ ጥጃ የመሆኑ ጉዳይ ቁጥጥሩና ክትትሉ የአንድ ሰሞን ጉዳይ ስለሆነ ነው ብል አልተሳሳትኩም፡፡

2.  መንጃ ፈቃድ

ብዙዎችሹፍርናኮ የመሃይም ሥራ ነውይላሉ፡፡ አባባሉ ለብዙ ጊዜያት አይገባኝም ነበር፣ በኋላ ነው እውነታው የተገለጠልኝ፡፡ ለካስ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት ብር እንጂ ዕውቀት እምብዛም ፋይዳ የለውምና፡፡

እኛ አገር የመንጃ ፈቃድ ለመያዝ ዋነኛው ነገር ዳጎስ ያለ ብር ነው፡፡ ዕውቀት ሁለተኛ ነገር ነው፡፡

የአውሮኘላን አብራሪ ለመሆን ግን ብር ሳይሆን ዕውቀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚያውም በእንግሊዘኛ፣ በሒሳብና ፊዚክስ ትምህርቶች ሰቃይ ተማሪ መሆን ይጠበቃል፡፡ ግና አውሮፕላንም የሰው ስሪት ነው፤ መኪናም የሰው እጅ ስራ ነው፡፡ አውሮፕላንም የሰው ነፍስ ይዞ ነው የሚጓዘው፣ መኪናም እንደዚያው፡፡ ታዲያ ለመኪናስ የአውሮፕላኑን ያህል ባይሆንም፣ ነገሩ የህይወት ጉዳይ ነው ተብሎ ለምን አልተካበደም ?. . .  የመኪና ቁጥር ከአውሮፕላን ቁጥር ስለሚልቅ ይሆን? . . . ወይስ የመኪና ከአውሮፕላን ዋጋ ሲነጻጸር ምንም ስለሆነ? . . . ነው ወይንስ ሌላ የማላውቀው ምክንያት ይኖር ይሆን?

3. ጫትና አልኮል

 ሌላኛው ምክንያት ጫትና አልኮል በመጠቀም የሚያሽከረክሩ ሰዎች ላይ ቁጥጥሩ በመላላቱ ነው፡፡ በተለይም ከምሽት ክለባትና ጭፈራ ቤቶች ተዝናንተው መሪ የሚጨብጡ ሰዎች፣ በሰው ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኅብረተሰቡ መገልገያዎች ላይ እያደረሱ ያሉት ጉዳት ይህ ነው አይባልም፡፡ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ የድልድይ ብረቶች፣ የትራፊክ ደኅንነት ምልክቶች፣ ወዘተ . . . አልኮልና ዕፅ ያደነዘዛቸው አሽከርካሪዎች ሰለባ ናቸው፡፡

ከዚህ ሁሉ ባሻገር ግን በአገራችን የትራፊክ ሲስተም ከተሰወሰነ ፍጥነት በላይ እና ጠጥተው ለሚያሽከረክሩ ሰዎች የራዳር መቆጣጠሪያ (radar guns)  እጥረት ወይም ከነጭራሹ አለመኖር ሌላው ተያይዞ የሚነሳ ደጋፊ ምክንያት ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማንና የክልል ከተሞችን የሚያማክልኮምፒዩተራይዝድ ኔትዎርኪንግአለመኖርም ችግሩን አብሶታል፡፡

4.  የሌት ጉዞ  

አራተኛው ምክንያት ሌሊት ሌሊት በሚጓዙ መኪኖች ላይ ቁጥጥር ማዕቀብ ባለመጣሉ ነው፡፡ በተለይም በዘልማድአባዱላየሚባሉት መኪኖች በአንድ ጉዞ ብቻ ከመነሻው ተነስተው መድረሻው ላይ መገኘት በመፈለጋቸው አደጋውን የከፋ አድርገውታል፡፡

አንድ ሰው መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ በፈለገበት አቅጣጫ ቢጓዝ፣ ፈንግል እንዳያዛት ዶሮ በየሰርጡና በየጉድባው፣ እዚህም እዚያም መኪኖች ተፈንግለው ቢያይ አይደንቅም፡፡

5.  የአሽከርካሪዎች ብስለት

 አምስተኛው ምክንያት፣ በአእምሯቸውና ዕድሜያቸው ያልበሰሉ ጨቅላ አሽከርካሪዎችመሪን ያህል ነገር በመጨበጣቸው ነው፡፡ በተለይም ከወላጆቻቸው መኪና ሰርቀው፣ ሰው አየኝ አላየኝ እያሉ በፍርሃትና በችኮላ እየተርበተበቱ የሚነዱ ልጆች አደጋውን እያባሱት ይገኛሉ፡፡

6.  ቅጥ ያጣ ድህነት

 ስድስተኛውና አንኳሩ ምክንያት መላቅጡን ያጣው ድህነታችን ነው፡፡ በትራንስፖርት እጥረት እንደ ሰርዲን ታጭቆ የሚጓዘው ህዝባችን ደግሞ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡

አንድ የመኪና ካምፖኒ መኪና ሲፈበርክ የጭነቱን ልክ ይወስናል፡፡ ማለት በሌላ አነጋገር ጭነቱ ከዚህ ካለፈ መኪናው አደጋ ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ይሁንና በኛው አገር ራሱ የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሻረው በሚመስለው ህጉ በተለይም በሃይገር ባሶች ላይ ይህ ነው የማይባል ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ተሳፋሪዎች ታጭቀው ሲታይአቤቱ ሰውረን ከመዓቱየሚለው ጸሎት ትውስ ይላል፡፡

7.  ሙስና

በትራፊክ ጉዳያችን ላይ ሥር ነቀል የሆነ ለውጥ ማምጣት ያልታቻለውና አደጋውን መቀነስ ያልተቻለው ሰባተኛው ምክንያት ሙስና ነው፡፡

ብዙ ሰዎች በተለይም ኪሳቸው የሚናገር፣ ብዙ ውጣ ውረድ ሳያዩ መንጃ ፈቃዱ ተሠርቶ ቤታቸው ድረስ ሊመጣላቸው ይችላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የፀረ ሙስና መርማሪ ኮሚሽን በነካ እጁወደ መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን /ቤት ጐራ ቢል አትርፎ የሚወጣ ይመስለኛል፡፡

 

በአጠቃላይ ያልተፈታው የትራፊክ ደኅንነት ጉዳያችን በሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ብቻ ሳይሆን የሚያደርሰው ሥነልቡናዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሱ የትየለሌ ነውና ጉዳዩ ጆሮ ዳባ ልበስ አይባልበትም፡፡

መኪና ስታሽከረክር ራስህን ከአደጋ ትጠብቃለህ?

ምንጭ ያልተገለጸ  ጽሁፍ

“እስከ ዛሬ ድረስ መኪና ሳሽከረክር አደጋ አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ስለዚህ አደጋ ይደርስብኛል ብዬ አልጨነቅም።” “አደጋ የሚደርስባቸው ያልበሰሉና ንዝህላል አሽከርካሪዎች ናቸው።” ብዙ የመኪና አሽከርካሪዎች አደጋ ይደርስብናል ብለው ፈጽሞ አያስቡም። አንተም የሚሰማህ እንደዚህ ነው? አደጋ ፈጽሞ አይደርስብኝም የሚል ስሜት አለህ?

በበለጸገ አገር ውስጥ የምትኖር ከሆነ በሕይወት ዘመንህ ቢያንስ አንድ ጊዜ የመኪና አደጋ ሊደርስብህ እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ። ብዙዎቹ አደጋዎች ሞት የሚያስከትሉ ናቸው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ከግማሽ ሚልዮን የሚበልጡ ሰዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጣሉ። ምናልባትም ባለፈው ዓመት በመኪና አደጋ ከሞቱት ውስጥ አብዛኞቹ እንዲህ ያለ አደጋ ይደርስብኛል ብለው ፈጽሞ አስበው አያውቁ ይሆናል። የመኪና አደጋ እንዳይደርስብህ ምን ማድረግ ትችላለህ? ቁልፉ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነው። እየነዱ ከማንቀላፋትና ከዕድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ የሚደርሱ አደጋዎችን እንዴት መከላከል እንደምትችል እስቲ እንመልከት።

እንቅልፍ የሚጫጫናቸው አሽከርካሪዎች

አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት እንቅልፍ ተጫጭኖት መኪና የሚያሽከረክር ሹፌር አደጋ የማድረስ አጋጣሚው ሰክሮ መኪና ከሚያሽከረክር ሹፌር ጋር እኩል ነው። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በእንቅልፍ ሳቢያ የሚደርሱት የመኪና አደጋዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በኖርዌይ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ12 አሽከርካሪዎች ውስጥ አንዱ እንቅልፍ እያዳፋው እንደሚያሽከረክር ፍሊት ሜንቴይናንስ ኤንድ ሴፍቲይ ሪፖርት በቅርቡ ባወጣው ዘገባ ገልጿል። በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ የሚታተመው ዘ ስታር የተባለው ጋዜጣ በዚያች አገር ውስጥ ከሚደርሱት የመኪና ግጭቶች ውስጥ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ሹፌሮች ደክሟቸው መኪና በመንዳታቸው ምክንያት የሚያጋጥም እንደሆነ ገልጿል። ከሌሎች አገሮች የሚወጡ ዘገባዎችም ድካም በማንኛውም ቦታ የሚገኙ አሽከርካሪዎችን ለአደጋ እየዳረገ እንዳለ ያሳያሉ። እንቅልፍ የሚጫጫናቸው አሽከርካሪዎች የበዙት ለምንድን ነው?

የምንኖርበት ጊዜ ሩጫ የበዛበት መሆኑ ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ አድርጓል። በቅርቡ ኒውስዊክመጽሔት ሪፖርት እንዳደረገው አሜሪካኖች “በየምሽቱ በእንቅልፍ የሚያሳልፉት ሰዓት በክፍለ ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ያሳልፉት ከነበረው በአንድ ሰዓት ተኩል እንደሚያንስና ወደፊትም ችግሩ ሊባባስ እንደሚችል” ዘግቧል። ለምን? መጽሔቱ በእንቅልፍ ዘርፍ ባለሙያ የሆኑትን ቴሪ ያንግን ጠቅሶ እንደተናገረው “ሰዎች ራሳቸውን እንቅልፍ ቢነፍጉ ብዙም እንደማይጎዱ አድርገው ያስባሉ። በቂ እንቅልፍ ሳያገኙ መሥራት የጠንካራ ሠራተኛነትና የእድገት ምልክት እንደሆነ ተደርጎ ይታያል።”

አንድ ሰው በየምሽቱ በአማካይ ከስድስት ሰዓት ተኩል እስከ ዘጠኝ ሰዓት ለሚያህል ጊዜ እንቅልፍ ማግኘት እንደሚያስፈልገው ይነገራል። ሰዎች ይህን ለሚያክል ጊዜ በየቀኑ ካልተኙ “የእንቅልፍ ዕዳ” ይኖርባቸዋል። የአሜሪካን የተሽከርካሪዎች ማኅበር የትራፊክ ደህንነት ተቋም ያሰራጨው አንድ ሪፖርት እንዲህ ይላል:- “ብዙም ሥራ በማይበዛበት ሳምንት በየምሽቱ ማግኘት ካለብህ እንቅልፍ 30 ወይም 40 ደቂቃ ያነሰ እንኳ ብትተኛ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ከ3 እስከ 4 ሰዓት የሚደርስ የእንቅልፍ ዕዳ ሊጠራቀምብህ የሚችል ሲሆን ይህ ደግሞ ቀን ላይ እንቅልፍ እንዲጫጫንህ ሊያደርግ ይችላል።”

አንዳንድ ጊዜ የእንቅልፍ ማጣት፣ የልጅ መታመም ወይም ሌላ ዓይነት ከባድ ችግር ጥሩ እንቅልፍ እንዳታገኝ ሊያደርግህ ይችላል። በሚቀጥለው ቀን መኪና ስትነዳ እንቅልፍ እንቅልፍ ሊልህ ይችላል። በዚህ ጊዜ ማድረግ ያለብህ ምንድን ነው?

ቡና በመጠጣት፣ የመኪናን መስኮት በመክፈት፣ ማስቲካ በማላመጥ ወይም ቅመም የበዛበት ምግብ በመመገብ የመጣብህን እንቅልፍ ለማባረር ብትሞክርም አንዳቸውም በንቃት እንድትነዳ አይረዱህ ይሆናል። ከእነዚህ ውስጥ የትኛውም ቢሆን ለችግርህ መፍትሔ አይሆንም። የሚያስፈልግህ መተኛት ብቻ ነው። ስለዚህ መንዳትህን አቁመህ ለምን አታሸልብም? ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንዲህ ይላል:- “ሰውነትህን ለማነቃቃት ብለህ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የምትተኛው እንቅልፍ ከ30 ደቂቃ መብለጥ የለበትም፤ ከዚያ ከበለጠ ሰውነትህ ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ይገባና ቶሎ መንቃት አስቸጋሪ ሊሆንብህ ይችላል።” ለጥቂት ደቂቃ አረፍ ብሎ ማሸለብ ጉዞህን ሊያዘገይብህ ቢችልም ሕይወትህን ሊያራዝምልህ ይችላል።

የአኗኗር ዘይቤህ መኪና ስትነዳ እንቅልፍ እንቅልፍ እንዲልህ ሊያደርግህ ይችላል። ኢንተርኔት በመጠቀም ረጅም ሰዓት ታሳልፋለህ? ወይስ ቴሌቪዥን በመመልከት እስከ ሌሊት ትቆያለህ? እስከ እኩለ ሌሊት በሚቆዩ ግብዣዎች ላይ ትገኛለህ? እንዲህ ዓይነት ልማዶች የእንቅልፍ ጊዜህን እንዲሻሙብህ አትፍቀድ። ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን በአንድ ወቅት ጥቂት ዕረፍት እንኳ ዋጋ እንዳለው አጉልቶ ተናግሯል።—⁠መክብብ 4:6

ልምድ ያካበቱ ሆኖም በእድሜ የገፉ

አብዛኛውን ጊዜ በዕድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች መኪና የመንዳት ልምድ አላቸው። በተጨማሪም አይዳፈሩም እንዲሁም አቅማቸውን ያውቃሉ። እንዲህ ሲባል ግን በእድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች የመኪና አደጋ አያጋጥማቸውም ማለት አይደለም። እንዲያውም እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ለእንዲህ ዓይነቱ አደጋ ይበልጥ የተጋለጡ ሊሆኑ ይችላሉ። ካር ኤንድ ትራቭል የተሰኘው በዩ ኤስ ኤ የሚታተም መጽሔት “እድሜያቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ከጠቅላላው ሕዝብ ውስጥ 9 በመቶ ብቻ ቢሆኑም በመኪና አደጋ ከሚሞቱት መካከል 13 በመቶ የሚሆኑት እነርሱ ናቸው” በማለት ዘግቧል። የሚያሳዝነው በእድሜ በገፉ አሽከርካሪዎች የሚደርሰው የመኪና አደጋ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።

የሰማንያ ዓመት አረጋዊ የሆኑት ሙርተል የሰጡትን አስተያየት ተመልከት።* መኪና መንዳት የጀመሩት የዛሬ 60 ዓመት ሲሆን አንድም ቀን አደጋ ገጥሟቸው አያውቅም። ሆኖም እንደሌሎቹ በእድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች ሁሉ እርሳቸውም ከዕድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ችግሮች እያጋጠሟቸው ነው። በቅርቡ ለንቁ! መጽሔት ሲናገሩ “እርጅና እየተጫጫነህ ሲመጣ በሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገሮች [መኪና መንዳትን ጨምሮ] ከባድ እየሆኑብህ ይመጣሉ” ብለዋል።

የመኪና አደጋ እንዳይደርስባቸው ምን አደረጉ? “ዓመታቱ እያለፉ ሲሄዱ እርጅና ያመጣብኝን የአቅም ገደብ ለማካካስ ማስተካከያዎችን አድርጌያለሁ” በማለት ሙርተል ይናገራሉ። ለምሳሌ ያህል መኪና መንዳትን በተለይ ደግሞ በምሽት መኪና በመንዳት የሚያሳልፉትን ጊዜ ቀነሱ። ይህ መጠነኛ የሆነ ለውጥ መኪና መንዳታቸውን ጨርሶ ማቆም ሳያስፈልጋቸው ከአደጋ ተጠብቀው መኪና ማሽከርከራቸውን እንዲቀጥሉ ረድቷቸዋል።

ለመቀበል የሚከብድ ቢሆንም እንኳ እርጅና የሚያስከትለው መዘዝ ሳይነካው የሚያመልጥ ማንም ሰው የለም። (መክብብ 12:1-7) በርካታ የጤና እክሎች ያጋጥማሉ፣ ቅልጥፍናችንና የማየት ችሎታችን በእጅጉ ይቀንሳል። እነዚህ ሁሉ ችግሮች መኪና መንዳትን አስቸጋሪ ያደርጉታል። ይሁን እንጂ የእድሜ መግፋት በራሱ አንድን አሽከርካሪ መኪና መንዳቱን እንዲያቆም አያደርገውም። ዋነኛው መለኪያ የአሽከርካሪው ቅልጥፍና ነው። በአካላዊ ሁኔታችን ላይ ያሉትን ለውጦች አምኖ መቀበልና በመኪና አነዳድ ልማዳችን ላይ አስፈላጊ ማስተካከያዎችን ማድረግ መኪና የማሽከርከር ብቃታችንን ሊያሻሽልልን ይችላል።

ልብ አላልከው ይሆናል እንጂ የማየት ችሎታህ እየቀነሰ ሊሆን ይችላል። እድሜህ እየገፋ ሲሄድ የእይታ አድማስህ እየጠበበ የሚሄድ ሲሆን በዓይንህ ውስጠኛ ክፍል የሚገኘው ሬቲናም ብዙ ብርሃን ማግኘት ይፈልጋል። ዚ ኦልደር ኤንድ ዋይዘር ድራይቨር የተባለው ቡክሌት እንዲህ ይላል:- “ስድሳ ዓመት የሆነው አንድ መኪና አሽከርካሪ በአሥራዎቹ እድሜ የሚገኝ አንድ ልጅ ለማየት ከሚያስፈልገው በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ብርሃን የሚያስፈልገው ሲሆን ከብርሃን ወደ ጨለማ ሲገባ ዓይኖቹን ለማለማመድ የሚወስድበት ጊዜ ከልጁ በሁለት እጥፍ ይበልጣል።” በዓይናችን ላይ የሚከሰቱት እነዚህ ለውጦች በምሽት መንዳትን ፈታኝ ሊያደርጉብን ይችላሉ።

ሄንሪ የ72 ዓመት አረጋዊ ሲሆኑ ለ50 ዓመታት ሲነዱ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው አያውቅም። ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ግን ምሽት ላይ ከፊት ለፊት የሚመጡ መኪናዎች የሚያበሩት መብራት ዓይናቸውን እያጥበረበረው መኪና መንዳትን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው አስተዋሉ። የዓይን ምርመራ ካደረጉ በኋላ ይህንን ብርሃን እንዲቀንስ ተደርጎ የተሠራ አዲስ ዓይነት መነጽር ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ተገነዘቡ። ሄንሪ “አሁን አለ ችግር በምሽት መንዳት እችላለሁ” በማለት ይናገራሉ። ይህን ትንሽ ማስተካከያ ማድረጋቸው ያለ ችግር መኪና መንዳት እንዲችሉ ረድቷቸዋል። እንደ ሙርተል ላሉት ሌሎች አሽከርካሪዎች ግን መፍትሔው በምሽት መኪና መንዳትን ፈጽሞ መተው ሊሆን ይችላል።

በተጨማሪም የዕድሜ መግፋት ፈጠን ብሎ እርምጃ ለመውሰድ እንቅፋት ይሆናል። አረጋውያን ከወጣቶች ይልቅ ብልህና አስተዋይ ሊሆኑ ይችላሉ። ቢሆንም አንድ ሰው ዕድሜው እየገፋ በሄደ መጠን በተመለከተው ወይም በሰማው ነገር ላይ አውጥቶ አውርዶ እርምጃ ለመውሰድ ከበፊቱ የበለጠ ጊዜ ይወስድበታል። ይህ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚለዋወጡት የትራፊክና የመንገድ ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ መኪና መንዳትን ለአረጋውያን ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል። አስፈላጊውን እርምጃ በወቅቱ ለመውሰድ እንዲቻል እነዚህን ለውጦች ወዲያውኑ ማገናዘብ ያስፈልጋል።

“በዕድሜ የገፉ አሽከርካሪዎች ከባድ አደጋ የሚደርስባቸው በአብዛኛው የትራፊክ ምልክቶችን ልብ ሳይሉ በመቅረታቸው ነው” በማለት ካር ኤንድ ትራቭል የተባለው መጽሔት ሪፖርት አድርጓል። ለምን? ይሄው ሪፖርት ሲቀጥል እንዲህ ይላል:- “ችግሩ . . . በዕድሜ የገፋው አሽከርካሪ ወደ መስቀለኛ መንገድ ከመግባቱ በፊት ከግራና ከቀኝ የሚመለከተውን ነገር በፍጥነት አገናዝቦ እርምጃ ከመውሰዱ ጋር የተያያዘ ይመስላል።”

ይህን ችግር ለማስወገድ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ወደ መስቀለኛ መንገዶች ስትቃረብ ጥንቃቄ አድርግ። መንገዱን ማቋረጥ ከመጀመርህ በፊት ግራና ቀኝህን ደጋግመህ የመመልከት ልማድ ይኑርህ። በተለይ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ በምትታጠፍበት ጊዜ ጥንቃቄ አድርግ። በመስቀለኛ መንገድ ላይ መታጠፍ በተለይ ደግሞ ከፊት ለፊት የሚመጡ መኪናዎች የሚያልፉበትን መንገድ ማቋረጥ የሚኖርብህ ከሆነ አደገኛ ሊሆን ይችላል።

በዩናይትድ ስቴትስ እድሜያቸው ከ75 ዓመት በላይ የሆኑ አሽከርካሪዎች በመስቀለኛ መንገድ ላይ ከሚደርስባቸው ከባድ አደጋዎች ውስጥ 40 በመቶ የሚሆኑት አሽከርካሪው ወደ ግራ ለመታጠፍ በሚሞክርበት ጊዜ የሚከሰቱ ናቸው። የአሜሪካን የተሽከርካሪዎች ማኅበር የትራፊክ ደህንነት ተቋም በዚያ አገር ለሚገኙ አሽከርካሪዎች “አንዳንድ ጊዜ ወደ ግራ መታጠፍን ለማስቀረት ሦስት ጊዜ ወደ ቀኝ ታጥፈህ ወደምትፈልግበት ቦታ መሄድ ይሻላል” በማለት ሐሳብ ያቀርባል። አንተም የምትኖርበትን አካባቢ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህን ዘዴ ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ። አስቀድመህ ካሰብክበት አደገኛና አስቸጋሪ የሆኑ መስቀለኛ መንገዶችን ከማቋረጥ ልትድን ትችላለህ።

ልታስብበት የሚገባ ውሳኔ

መኪና የመንዳት ችሎታህን ለመመዘን ምን ልታደርግ ትችላለህ? የምትቀርበው ጓደኛህ ወይም የቤተሰብህ አባል አብሮህ እንዲጓዝ በማድረግ የመንዳት ችሎታህን እንዲገመግም ልትጠይቀው ትችላለህ። ከዚያም የሚሰጥህን ሐሳብ በጥንቃቄ አዳምጥ። እንዲሁም መኪና የመንዳት ችሎታን ለማሻሻል የሚሰጡ ትምህርቶችን መውሰድ ትችላለህ። በአንዳንድ አገሮች የሚገኙ የአሽከርካሪዎች ማኅበራት በዕድሜ ለገፉ አሽከርካሪዎች ልዩ ሥልጠና ይሰጣሉ። አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ለጥቂት ከአደጋ ከተረፍክ የመንዳት ችሎታህ እንደድሮው እንዳልሆነ የሚያሳይ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል።

እድሜህ እየገፋ ሲሄድ መኪና መንዳት ማቆም እንዳለብህ መወሰንህ አይቀርም። እንዲህ ያለውን ውሳኔ ማድረጉ ከባድ ሊሆን ይችላል። ቀደም ሲል የተጠቀሱት ሙርተል አንድ ቀን መኪና ማሽከርከር እንደሚያቆሙ ያውቃሉ። እስከዚያው ግን ሌሎች በሚነዱት መኪና መጓዝን ማዘውተር ጀምረዋል። ሌላ ሰው እንዲነዳላቸው በማድረጋቸው ምን ይሰማቸዋል? “መኪና መንዳት የሚያስከትለው ውጥረት ሳይሰማህ መጓዝ ደስ የሚል ነው” በማለት ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ በጥንቃቄ ካሰብክበት በኋላ አንተም እንዲህ ማድረግ እንዳለብህ ይሰማህ ይሆናል። ከጓደኛህ ጋር ሆነህ ገበያ መውጣት፣ አንዳንድ ጉዳዮችን ማስፈጸምና ወደ ቀጠሮ ወይም ወደ ስብሰባ ቦታ መሄድ ይበልጥ አስደሳች ሊሆንልህ ይችላል። ምናልባትም ጓደኛህ መኪናህን እየነዳልህ አብረኸው ልትሄድ ትችላላችሁ። ብቻህን ከመንዳት ይልቅ ከሰው ጋር መሆኑ ይበልጥ አስተማማኝና አስደሳች ሊሆን ይችላል። በሕዝብ መጓጓዣ መጠቀምም ሌላው አማራጭ ነው። ማንነትህ የሚለካው መኪና በመንዳት ችሎታህ እንዳልሆነ አስታውስ። በቤተሰብህ፣ በጓደኞችህ እንዲሁም በአምላክ ፊት ዋጋ እንዲኖርህ የሚያደርጉት መልካም ባሕርያትህ ናቸው።—⁠ምሳሌ 12:2፤ ሮሜ 14:18

ወጣትም ሆንክ በእድሜ የገፋህ፣ ልምድ ያካበትክ አሽከርካሪም ሆንክ ገና ለማጅ የመኪና አደጋ እንደማይደርስብህ አድርገህ ፈጽሞ ማሰብ አይኖርብህም። መኪና ማሽከርከር ከባድ ኃላፊነት እንደሆነ አስታውስ። ሊያጋጥምህ የሚችለውን የመኪና ግጭት ለመቀነስ ጥንቃቄ አድርግ። እንዲህ በማድረግ ወደፊት በምታደርጋቸው ጉዞዎች ላይ የአንተንም ሆነ የሌሎችን ሕይወት መጠበቅ ትችላለህ።

Sunday, 21 February 2016 01:00

አደጋውና ማስጠንቀቂያው

አደጋውና ማስጠንቀቂያው


ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሆድ ዕቃ የመጎብኘት ዕድል አግኝቼ ነበር፡፡ አየር መንገዱ ያስመረቀውን ዘመናዊ ኮሌጅ በማስመልከት የአየር መንገዱን ነገረ ሥራ እንድንጎበኝ ተጋብዘን ነበር፡፡ የጥገና ቦታውን፣ የካርጎ ማዕከሉን፣ አዳዲስ እያስፋፋቸው የሚገኙ የካርጎና የጥገና ቦታዎችን አይተናል፡፡ የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ ለሚመለከት ሰው ከጥንት ጀምሮ እየካበት፣ እየተሳለጠና እየሠለጠነ የመጣውን ይህን ታላቅ ሀገራዊ ድርጅት እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ ለመረዳት ያስችለዋል፡፡ እንዲያውም እኛ ሀገር እንደ አበሻ መደኃኒት ሁሉም ነገር ምሥጢር ስለሚሆን ነው እንጂ ልጆቻችን በጉብኝት ፕሮግራሞች የአየር መንገዱን የሆድ ዕቃ የማየት ዕድሉ ቢኖራቸው ኖሮ አየር መንገዱንም እንዲወዱ የፈጠራ ፍልጎታቸውም እንዲጨምር ያደርገው ነበር፡፡
በጥገና ክፍሉ የጀመረው ጉብኝት በካርጎ ክፍሉ በኩል አድርጎ በአዳዲስ የማስፋፋያ ፕሮጀክቶቹ በኩል ሲጠናቀቅ ዓይኔ አንድ ነገር ላይ ዐረፈ፡፡ ነገሩ የተጻፈው በአየር መንገዱ የጥገና ክፍል ግድግዳ ላይ ነው፡፡ ለእኔ ከጥገና መሣሪያዎች፣ ከጠጋኞቹ ብቃትና ለጥገና ብቃቱ የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ከሰጡት ዕውቅና ባልተናነሰ የሳበኝ በየግድግዳው የተለጠፉት የደኅንነት ማሳሰቢያዎቹ ናቸው፡፡
‹አደጋውን ሪፖርት ከማድረግህ በፊት ምልክቱን ቀድመህ ተናገር - report a hazard before you have to report an accident› ይላል፡፡ በዚያ ፈረስ በሚያስጋልብ የጥገና አዳራሽ ውስጥ የተለያዩ አደጋዎችን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ምልክቶች በመብራት አማካኝነት ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላለፉ ተደርገዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የማስጠንቀቂያ እሪታ (ሳይረን) ያሰማሉ፡፡ እነዚህን የአደጋ ምልክቶች ቀድሞ ማወቅና ለእነዚህ ምልክቶችም ተገቢውን ምላሽ መስጠት በኋላ ለአደጋው ምላሽ ከመስጠት ያድናል፡፡ ጎበዝ ባለሞያም የደረሰውን አደጋ ሳይሆን አደጋ እንደሚመጣ የሚገልጠውን ማስጠንቀቂያ ቀድሞ ይናገራል፡፡ ይኼ ነው የጥገና ክፍሉ ግድግዳ ላይ በትልቁ የተሰቀለው፡፡
በሀገራችን ‹በዕንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ›፣ ‹ጢሱን አይተህ እሳቱን፣ ቀንዱን አይተህ ከብቱን ተጠንቀቅ›፣ ‹በቅርቡ ያልመለሰ እረኛ፣ በሩቁ ሲባዝን ይኖራል›፣ ‹ውሻውን አይተህ ካልተደበቅክ አዳኙ አይቶ ይገድልሃል›፣ ‹አውው ሲል ዝም ካልክ ‹አሙሙ ብሎ ይገምጥሃል› የሚሉ የዚህ ምክር ጓደኞች ሞልተዋል፡፡ ውሻ ለአህያ ‹የመጀመሪያው መጥሪያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ነው› ብሎ የመከረው ምክር የዚህ ማስጠንቀቂያ አንድምታ ትርጓሜ ውስጥ ‹ታሪክ አንደ አህያ ነው› ተብሎ ተካትቷል፡፡ ታሪኩስ እንደምን ነው ቢሉ አህያና ውሻ መንገድ ዘመቱ አሉ፡፡ ከዘመቻ ሲመለሱ መሸባቸውና ውሻ የሚበላ አጥቶ ተኮራምቶ ሲተኛ አህያ ግን መስኩ ላይ ያገኘቺውን ሣር ግጣ ሆዷ ተነፋ፡፡ ‹ከተራበ ይልቅ ለጠገበ አዝናለሁ› እንዲል ሕዝቡ፡፡ ይህስ ስለምን ነው ቢሉ የጠገበ ሰው ረሐብ ያለ አይመስለውም፡፡ የተራበ ተጠቅልሎ ሲተኛ የጠገበ ግን የተጠቀለለውን እየፈታ እንደ አጤ ልብነ ድንግል ጦር አውርድ ይላል፡፡
እናም አህያ ከጥጋቧ ብዛት ‹ልጩህ› አለች፡፡ ውሻ ‹ለምን› ቢላት ‹ፎረሸኝ› አለች፡፡ ‹ፎረሸኝ ማለትስ ምን ማለት ነው ቢሉ፡፡ ጥጋቤ ቅጥ አሳጣኝ፤ ከትዕቢት አላግቶ ምን ይመጣል አስባለኝ፣ የጠገበ ሲጮኽ የተራበ እንደሚበላው እንዳላውቅ አደረገኝ› ማለት ነው፡፡ እናም አህያዋ ልትጮህ ስትል ‹ተይ ይቅርብሽ ጅብ ይሰማሻል› አላት ውሻ፡፡ ከጠገቡ አያስቡ፣ ከወፈሩ ሰው አይፈሩ፣ ከተበቱ አይታይ ሥጋቱ፣ እንዲል መጽሐፈ ባልቴት፡፡ ‹ተው ባክህ፤ የት አግኝቶ ይሰማኛል› አለቺው፡፡ ‹እንዴ ይኼኮ የጅብ አገር ነው፡፡ የተራበ ጅብ የጠገበ አህያ መስማት እንዴት ያቅተዋል› አላት፡፡ ‹ባክህ ቢሰማስ ምን ያመጣል› አለቺና አናፋች፡፡ ‹ምን ያመጣል ብሎ ገብቶ፣ ማን ያወጣል ብሎ ጮኸ› እንዲል ነገረ ሕዝብ፡፡
ጅብ ልጁን እየላጨ ነበር አሉ፡፡ ሰማ፡፡ ግን የድምጹን አቅጣጫ ለማወቅ አልቻለም፡፡ አህያም ብትጠብቅ ብትጠብቅ የመጣ ጅብ የለም፡፡ ውሻውንም ‹ባክህ ዝም ብለህ ሽብር ስትነዛ ነው እንጂ፤ ጅቡ ወይ ሞቷል፣ ወይ የለም፣ ወይ ተኝቷል› አለቺው፡፡ ‹አይደለም› አለ ውሻ፡፡ ‹አይደለም፤ ጅቡ ሰምቷል፡፡ አንቺ ግን መስማቱን ማወቅ አልቻልሽም፡፡ አሁንም በዚህ ቢበቃሽ ጥሩ ነው› አላት፡፡ ‹ጥጋበኛ ሰው ሦስት ነገሩ ይወፍራል - ጆሮው፣ ዓይኑና ልቡ› ይላል መዝገበ ጠቢባን፡፡ ጆሮው ከራሱ በቀር እንዳይሰማ ሆኖ፣ ዓይኑም ከራሱ በቀር እንዳያይ ሆኖ፣ ልቡም ቢያይም ቢሰማም እንዳያስተውል ሆኖ ጥጋብ ይደፍነዋል፡፡ እነዚህ በጥጋብ ሲደፈኑ ደግሞ ‹ኩራትና ትዕቢት› ዓይንና ጆሮ ይሆናሉ፡፡ ከዚያም
ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
ከመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ፡፡ የሚለው ትንቢታዊ ግጥም እስኪደርስባቸው ድረስ እንደ ኤድስ ማስታወቂያ ‹አላይም፣ አልሰማም እያሉ መኖር ነው፡፡
አህያ አሁንም መስኩን ብቻዋን ይዛ ትገሸልጠው ጀመር፡፡ መስክ ብቻን መያዝ ጥጋብ ያመጣልና ልቧ ተነፋ፡፡ ልቡ የተነፋ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መጮኽ ይወዳልና ‹ልጩህ› አለቺ፡፡ ውሻ ‹ተይ ይቅርብሽ ቅድም የታገሰሺን ጅብ ትእግሥቱን አታስጨርሺው› አላት፡፡ ‹ባክህ ምንም አያመጣም› አለቺና አናፋች፡፡ ‹አናፋች› ማለትስ ምንድን ነው ቢሉ ‹እንዳመጣላት ጮኸች፣ ደነፋች፣ ያዙኝ ልቀቁኝ አለቺ› ማለት ነው፡፡ ልጁን ሲላጭ የነበረው ጅብ አሁን አቅጣጫውን ለየና ወደ አህያዋ ዘንድ መምጣት ጀመረ፡፡ ነገር ግን አቅጣጫውን እንጂ ቦታውን አላገኘውም፡፡ ‹አቅጣጫውን እንጂ ቦታውን አላገኘውም› ሲል ምንድን ነው? ቢሉ ‹ሆዱ ግም ግም ብሏል፣ ልቡ ቱግ ቱግ ብሏል፣ መፍትሔው ጠፍቶበት እንጂ ችግሩን ለይቷል› ማለት ነው፡፡
አህያም እንደለመደቺው ብቻዋን በመስኩ ላይ ተለቀቀቺበት፡፡ ውሻ ግን ምንም አብሮ ቢዘምት እንደ አህያ የሚበላ አላገኘም፡፡ የተረፈው የዘመቻው እንጉርጉሮ ነው፡፡ ያንን እያንጎራጎረ ተኛ፡፡ ምንም ባዶ ሆድ ባያስተኛ፡፡ አህያ ግን ድጋሚ ፎረሻት፡፡ ‹ልጮህ ነው› አለቺው፡፡ ‹ይቅርብሽ፣ አሁን ሲሆን ልብ፣ ካልሆነም አደብ ግዢ፤ የመጀመሪያው መጥሪያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ነው› አላት፡፡ ሲጠግቡ እንጀራ ወደ ሆድ እንጂ ነገር ወደ ልቡና አይገባምና አልሰማቺውም፡፡ ‹ሰሚ ስታገኝ ተናገር፣ ዳኛ ስታገኝ መስክር› ነውና ዝም አላት፡፡ አህያም ጥጋብ አህያ መሆንዋን አስረስቷት ነበርና ለሦስተኛ ጊዜ አናፋች፡፡ ያን ጊዜ ቦታው ጠፍቶት ሲያደፍጥ የነበረው የተራበ ጅብ ከኋላዋ ቦትርፎ አህያ መሆንዋን እንድታውቀው አደረጋት፡፡ ችግሩ አህያነቷን ያወቀቺው ከተበላች በኋላ ሆነ፡፡
ያን የአየር መንገዱን የጥንቃቄ ማስታወቂያ እዚያ መስክ ላይ በአህያኛ የለጠፈላት ቢኖር፣ እርሷም የመስሚያ ጆሮና የመስማሚያ ልብ ቢኖራት ኖሮ በተረፈች ነበር፡፡ ከእርሷ በፊት እንደ እርሷ የመሰለ ነገር የገጠማት ቀበሮ ከአደጋው በፊት በማስጠንቀቂያው ተርፋለች ተብሎ በእንስሳት ታሪከ ነገሥት ውስጥ እንዲህ ተመዝግቧል፡፡ አንበሳ ታምሜያለሁ ብሎ በተኩላ በኩል እያስነገረ እንስሳቱ ሁሉ ሊጠይቁት ሲሄዱ በክርኑ ደቁሶ ይበላ ጀመር፡፡ በኋላ መተኛት ሰልችቶት ከአልጋው ተነሣና ምስጢሩን እንዳታወጣ ተኩላን አንገቷን ይቀነጥሳታል፡፡ አንበሳ ጫካ ውስጥ ሲመላለስ ቀበሮን ያገኛታል፡፡ ‹እፈልግሻለሁ› እያለ ይቀጥራታል፡፡ ትጠፋበታለች፡፡ ይቀጥራታል፤ ትጠፋበታለች፡፡ አንድ ቀን አሳቻ ቦታ አገኛትና ‹ለመሆኑ ለምን እንደምፈልግሽ በምን ዐውቀሽ ነው የምትጠፊው› ይላታል፡፡ ‹እኔማ በምን ዐውቃለሁ፤ ከተኩላ ጭንቅላት ተምሬ ነው እንጂ› አለቺው አሉ፡፡ ካለፉት ስሕተት የማይማር ያን ስሕተት ለመድገም የተረገመ ይሆናል፡፡ የታሪክ አንዱ ጥቅሙ ከአደጋው በፊት በምልክቱ እንድንነቃ ለማድረግ ነውና፡፡ ያለፉንን ሰዎች ስንወቅስ ከመኖር የተወቀሱበትን መረዳቱ ይበልጥ ይጠቅም ነበር፡፡
ቅሬታዎችን ማዳመጥ፣ ችግሮችን በጊዜ መፍታት፣ ለጥቃቅኑ ጉዳዮች ቀድሞ ትኩረት መስጠት፣ ጢሱን ሲያዩ እሳቱ እንደሚከተል መገመት፣ ከአደጋው በፊት በማስጠንቀቂያው ለመንቃት ያስችላል፡፡ የተናቀ ባቄላ ሆድ ይጎጥራል፡፡ ቻይኖች ጠብታ ውኃ እድሜዋ ከረዘመ ዐለት ትሰብራለች ይላሉ፡፡ ዝሆን አደን ሲሄድ ትንኞች የተሰበሰቡበት ሥፍራ ደረሰ፡፡ ሚስቱ ‹እኔ ይሄ ነገር አላማረኝም እንመለስ› አለቺው፡፡ ዝሆኑም ‹ለትንኝ ብለን› ይላትና ዝም ብሎ ይሄዳል፡፡ አንዷ ትንኝ ጆሮው ውስት ትገባና ትጮህበት ጀመር፡፡ ያ እንደ ሰፌድ የሰፋ ጆሮው መልሶ ድመጽዋን ሲያስተጋባለት የትንኟ ጩኸት እንደ ፈንጅ ድምጽ እየተሰማው ያስሮጠው ጀመር፡፡ ሚስቱ ተው ስትለው አልሰማ ብሎ የነበረው ዝሆን ትንኝ እያስጮኸቺ መንደሩ ደረሰ፡፡ ለደግነት እንጂ ለክፋት የሚያንስ የለም፡፡
የመሪዎች፣ የመንግሥታትና የድርጅቶች ታላቅነት የሚለካው ከአደጋው በፊት ለማስጠንቀቂያው በሚኖራቸው ዝግጅት ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን የመጀመሪያው መስሚያ፣ ሁለተኛው መቅረቢያ፣ ሦስተኛውም መበያ ይሆናል፡፡
Page 1 of 15
You are here: Home Menu Seyfu Mekonen