የመስሪያ ቤት[ቢሮ] ደህንነት

Written by  Sunday, 05 April 2015 15:46
Rate this item
(0 votes)

 

የመስሪያ ቤት ደህንነት

 

ከባድ ማሽኖችና መሳሪያዎች እንዲሁም የጉልበት ስራተኞች ባሉበት የስራ አካባቢዎች የጤንነትና የደህንነት ስጋት እንደሚኖር ይታወቃል፡፡

አብዛኛው ስራ የሚሰራው በመስሪያ ቤት ቁጭ ተብሎ የአየር ሁኔታ ሳያስቸግር ከሆነ ግን የደህንነት ስጋቱ ይቀንሳል፡፡ ሆኖም በመስሪያ ቤት ውስጥም በሚገርም ቁጥር የደህንነት ስጋት የሆኑ ነገሮች ይገጥማሉ፡፡

 የሰራተኞችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምንጮች እንደሚያመለክቱት  በአመት 80,000 የሚሆኑ የግል መስሪያ ቤት ሰራተኞችና ስራ አስኪያጆች በስራ ላይ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ ስለሆነም ሰራተኞች ወይም የሰራ ኃላፊዎች ችግሩን በጊዜ ቢደርሱበት ኖሮ ችግሩ ብዙ ጉዳት ሳያደርስ ማስቀረት ይቻል ነበር፡፡

የመስሪያ ቤት ሰራተኞችን ጉዳት ለመቀነስ የሚከተሉትን 11 ነጥቦች ይመልከቱ፡፡

 

መውደቅ

መንሸራተት፣ መደናቀፍና መውደቅ በመስሪያ ቤት ውስጥ በጣም የተለመዱ ጉዳቶች ናቸው፡፡ ኣንዳንድ ዘገባዎች  እንደሚሉት ሰራተኞች ከሌላ ቦታ ይልቅ በቢሮ ውስጥ መውደቅ ብቻ በ2.5 እጥፍ የአካል መጉደል ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ ስለሆነም ሰራተኞችን ግንዛቤ በመስጠት አብዛኞቹን ጉዳቶች መቀነስ እንችላለን፡፡

             

                

መተላለፍያን ነፃ ማድረግ

ካርቶኖች፣ ፋይሎችና ሌሎች በመተላለፍያ መንገድ ላይ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ዕቃዎች የመውደቅ አደጋ ያደርሳሉ፡፡  

 መተላለፍያ መንገድ ላይ ያሉ ዕቃዎች ሁሉ በተመደበላቸው ቦታቸው እንደተቀመጡ እርግጠኛ መሆን፡፡ የኤሌክትሪክ ገመዶች በመተላለፍያ ቦታዎች ላይ ከተዘረጉ የመውደቅ አደጋን ያመጣሉ፡፡ ስለሆነም በትክክልና በአግባቡ በመተላለፍያ ቦታ ላይ ሳይሆን ሰዎች በማይደርሱባቸውና ተገቢ በሆነ ቦታ ላይ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡

 

ከፍ ያሉ ነገሮች ላይ መውጣት (መቆም)

መቀመጫዎች ላይ መቆም፡- በተለይ ተሽከርካሪ የቢሮ መቀመጫዎች ከሆኑ ከባድ የመውደቅ አደጋ ያመጣል፡፡ ሰራተኞች ከፍ ካለ ቦታ ላይ ዕቃ ለማውረድ ሲፈልጉ መሰላል (stepladder) መጠቀም አለባቸው፡፡ መሰላሉ እስከመጨረሻው ከተከፈተ በኋላ በትክክለኛው ርቀት ላይ መሆኑንና እንዲሁም ሙሉ በመሉ መሬት ላይ መቀመጡን ማረጋገጥ፡፡ ሰራተኞች ከተፈቀደው ርቀት በላይ  ከፍ ማድረግ የለባቸውም፡፡

 

መተላለፍያዎች ለዓይን የሚታዩ (ብርሃን ያላቸው) ይሁኑ

ሰራተኞች ጨለም ባለ ኮሪደር ሲሄዱ ወይም ሲጠመዘዙ ሊጋጩ ይችላሉ፡፡ ኮንቬክስ መስተዋት (convex mirrors) ከተተከለ ግን ሰራተኞች በመጠምዘዣ ቦታዎች ላይ ማን እንደሚመጣ ስለሚታያቸው የመጋጨት አደጋዎች ይቀንሳሉ፡፡

 

ጭብጥ ያዙ

ምንጣፍ ማንጠፍ የመውደቀን አደጋ ይቀንሳል፡፡ ሊሾና እምነበረድ ወለሎች ስለሚያንሸራትቱ በተለይ እርጥብ በሚሆኑ ሠዓት ከባድ አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ በመግቢያዎች አካባቢ ምንጣፍ ማንጠፍ ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰራተኞች ወደ ስራ በሚመጡ ሰዓት ጭቃ (እርጥበት) ወይም ዝናባማ የአየር ሁኔታ ሊያጋጥማቸው ስለሚችል እርጥበቱን በጫማቸው ይዘው ይመጣሉ፡ ስለሆነም በሚገቡበትና በሚወጡት አካባቢ ምንጣፍ ቢነጠፍ ይመረጣል፡፡(ወይም የጫማቸውን ጭቃና እርጥበት የሚያስወግዱበት ምንጣፍ መሰል ነገሮች ቢዘጋጁ)።

ከዋናዎቹ የመስሪያ ቤት አደጋዎች ውስጥ ሌላኛው ሰራተኞች በሰራ ቦታ ላይ መውጫ በማጣት የሚያዙበት ነው፡፡   ከ15 ሺህ በላይ እንደዚህ ዓይነት ጉዳቶች ወይም አደጋዎች በ2007 ዓ.ም ደርሰዋል፡፡

 

መሳቢያዎችን መዝጋት

ፋይልና ብዙ እቃ የሞሉ መሳቢያዎች ተጠቅመን ካልዘጋናቸው ጉዳት ሊያደርሱና ዕቃዎቹ ወይም ፋይሎቹ ሊፈሱ ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ የተከፈቱ ማሳቢያዎች ሰራተኞችን የመውደቅ አደጋ  ወይም የመፈንከትና የማድማት ኣደጋ ሊያደርሱባቸው  ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ከተጠቀሙ በኋላ መሳቢያዎችን መዝጋትዎን አይርሱ፡፡

 

ዕቃዎችን አደጋ እንዳያደርሱ በስርዓቱ ማስቀመጥ

 ትላልቅ እቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ቢኖር በመስሪያ ቤቶች የሚፈጠረውን አደጋ ይቀንሳል፡፡ ብዙና ትልልቅ እቃዎች በግምጃ ቤት ካልተቀመጡ ከባድ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ከባድ እቃዎች ሲቀመጡ ማስቀመጫቸው ለመሬት የቀረበ መሆን አለበት፡፡

 

በአካባቢው አለመመቻቸት የሚደርስ ጉዳት

ምናልባት በመስሪያ ቤቶች የተለመደ ጉዳት ቢኖርና ቢደጋገም  የስራ አካባቢው ባለመመቻቸቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰራተኞች አብዛኛውን ሰዓታቸውን በመስሪያ ቤት ጠረጴዛ ላይና ኮምፒውተር ላይ ቁጭ ብለው እየሰሩ ስለሚያሳልፉ ይህን ተከትሎ የሚመጣ ጉዳት ወይም ህመም ቢኖር የስራ ቦታው የተመቸ ኣለመሆኑን አመላካች  ነው፡፡ ስለሆነም  የመውደቅ አደጋ ወይም ከቅርፃቸው ጋር በተያያዘ ወይም ከአየር ሁኒታ ጋር በተያያዘ ጉዳት  ያጋጥማቸዋል፡፡ ነገር ግን ከቦታ ባለመመቻቸት ምክንያት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን መከታተል ከባድ ነው፡፡    

 

እንደአስፈላጊነቱ የሚስተካከሉ እቃዎችን ማቅረብ

ወንበሮች፣ጠረጴዛዎች፣ የኮምፒውተር ማቆሚያዎች( እስታንዶችና) የመሳሰሉት እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከሉ መሆን አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የሰራተኛውን ሰፊ ቦታ በስርአቱ መጠቀም እንዲቻል ሲሆን እቃዎቹ  በማይስተካከል አሰራር ወይም በአንድ ወጥ መጠን ከተሰሩ የቢሮው ቦታ ላይበቃው ይችላል፡፡  ምናልባት ሰራተኞች ውድ የሆኑ ለማስተካከል የማይመቹ ዕቃዎችን መግዛት ላይስማሙ ይችላሉ፡፡ ግን ሞያተኞች እንደሚናገሩት ውድ ቢሆንም እንኳ እቃዎቹን መግዛት አስተዋይነት ነው፡፡ ጥሩ መቀመጫ በ5000 ቢሸጥ ጥሩ ኮምፒዩተር በ50 ሺህ ቢሸጥ  ነገር ግን የስራ አካባቢ ምቾት  (ergonomist) ባለሙያና ከስራ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች (occupational) የስነ ልቦና ሀኪሞች እንደሚሉት እነዚህ እቃዎች ባለመገዛታቸው ምክንያት የሚመጣው የጤና መታወክ እቃዎቹን ከሚገዙበት ብር በላይ መታከምያው ይፈጃል። ቀለል ባለ ገንዘብ የገዛናቸው እቃዎች ለጢና ተስማሚ ሳይሆኑ ቀርተው ጉዳት ያስከትሉና ለህክምና ብዙ ገንዘብ  ከማስወጣቱም በላይ ከስራ መቅረትና መባረርን ያስከትላል፡፡ በዚህም ተፈላጊና ቁልፍ ባለሙያን ማጣትም አለ።

 

 ሰራተኞች መሣሪያዎችን (equipment) እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው

እንደየአስፈላጊነቱ የሚስተካከሉ እቃዎች እንዲሁም መሳሪያዎች ማቅረብ የተመቻቸ የስራ አካባቢን ለመፍጠር የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ እኔ ግን እንደ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ያየሁት ሰራተኞች የቢሮአቸውን መቀመጫ ማስተካከል እንኳን አለመቻላቸው ነው፡፡  የሲፍቲ ሰዎች እንደሚሉት ብዙ ጊዜ አሰሪዎች እስከ 10'000 ብር አውጥተው ቆንጆ መቀመጫ ይገዛሉ ግን እንደዚህም ሆኖ ሰራተኞች መቀመጫቸውን የሚያስቀምጡበት ቦታ ላይስማማው ወይም ላይመጥነው ስለሚችል ሰራተኞቹ ሳይመቻቸው ይሰራሉ፡፡ ምክንያቱም ሰራተኞች ዕቃዎችን እንዴት መስተካከል እንዳለባቸውና የስራ አካባቢን ጠቃሚ በሆነ ሁኔታ እንዴት እንደሚመቻች ስለማያውቁ፡፡ ስለሆነም ሰራተኞችን ማለማመድና እነዚህን ጥቃቅን ስራዎች በደንብ እንዲያውቁና ራሳቸው መተግበር እንዳለባቸው ማድረግ፡፡  

 

እግርዎን መሬት ላይ ያስቀምጡ

በመጀመሪያው ጥያቄ (ethiosafety) ሰራተኞችን ወንበር ላይ ተቀምጠው ሲሰሩ እግራቸው መሬት ላይ ያርፍ እንደሁ ጠየቃቸው፡ በጣም ቀላል ጥያቄም ነው፡፡ ሆኖም አብዛኞቹ ሰራተኞች ኪቦርዳቸውን ከዲስክቶፕ ጋር ያስቀምጡትና ኪቦርዱ ላይ ለመድረስ ወንበራቸውን ከፍ ያደርጉታል፡ ስለዚህ እግራቸው መሬት አይነካም፡፡ የሰራተኞች እግር መሬት ላይ ካልተቀመጠ ወንበሩ  ህመምና አለመመቸትን ሊያስቆም አይችልም፡፡ ስለሆነም የኪቦርድና የኮምፒውተር ማስቀመጫው እንደአስፈላጊነቱ የሚስተካከሉ ከሆኑ ግን ሰራተኞች በሚፈልጉት ርቀትና በሚመቻቸው ቦታ ከፍ ዝቅ ማድረግ  ወይም ማሽከርከር እንደሚመቻቸው አስተካክለው መጠቀም ይችላሉ፡፡ የእግር ማሳረፍያን መጠቀም ሁለተኛ ምርጫ ሲሆን  የሰራተኞችን እንቅስቃሴ ሊያግድ ይችላል፡፡

 

የዶክመንት ማስቀመጫዎችን ማቅረብ

አንድ ሰራተኛ በተደጋጋሚ ከወረቀት ላይ ወደ ኮምቲውተር ያለእረፍት የሚፅፍ ከሆነ ወይም ስራው ኮምቲውተር ላይና ጠረጴዛ ላይ ማቀርቀር ከሆነ የአንገት ህመም ያጋጥመዋል፡፡   ራቅ ብለው የተቀመጡ ዶክመንት ማስቀመጫዎችን ማቅረብ ግን ይህንን ችግር ያቃልላል፡፡ እነዚህ የዶክመንት ማስቀመጫዎች አነስተኛና ተመጣጣኝ ዋጋ ነው ያላቸው፡፡ የዶክመንት መያዣዎቹ ቀኑን ሙሉ አቀርቅሮ ከመስራት የሚመጡ የአንገትና የጡንቻ ህመምን ይቀንሳሉ፡፡ የዶክመት መያዣዎች ዓይንም እንዳይጎዳ ይጠቅማሉ፡፡ ምክንያቱም ኮምፒውተር ላይ በምንሰራ ሰዓት ዶክመንት ለመፈለግ ወይም ለማስቀመጥ ዓይናችንን ከኮምፒውተር አንስተን ወደዶክመንቱ ስለምናደርግ፡፡ ኣሳማኝ ያልሆነ ሊመስል ይችላል።ግን በጣም ጠቃሚ ነው። በየእረፍት ሰኣቱም ለኣንገትና ለኣይን የሚስማሙ ቀላል የኣካል እንቅስቃሲዎችንም ማድረግ ብልህነት ነው።

 

የማውዝን አቀማመጥ ማስተካከል

Ethio safety ብዙ የስራ ቦታዎችን ሲመለከት ኪቦርዱ መቀመጫው ላይ ይቀመጣል፡ ማውዙ ግን ጠረጴዛ ላይ ነው የሚደረገው፡፡ ስለሆነም ከባድ የአንገትና በማውዙ በኩል ያለው ጫንቃ (ኣብዛኛውን ቀኝ ጎን) ህመምን ያስከትላል፡፡ ስለሆነም ማውዙ ከኪቦርዱ ጎን መቀመጥ አለበት ፡፡

 

አስፈላጊ ነጥቦች

የመውደቅ አደጋ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ እንዲሁም በስራ ቦታ መውጫ በማጣት በአንድ ነገር ላይ መያዝና ባልተመቻቸ የስራ አካባቢ የሚፈጠሩ አደጋዎች፡

በስራ ቦታ አካባቢ የተወሰነ መስተካከል ቢደረግ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡

 አስተዳደራዊ አገልግሎት፡-  በእቅድ መጓዝና መደበኛ የሆነ የሪፖርት አቀራረብ መዘርጋት የተመቻቸ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ይጠቅማል፡፡

 

መስሪያ ቤትዎን ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ ለማድረግ የሚጠቅሙ የተወሰኑ ነጥቦች

በቢሮ ውስጥ ማን እንደሚገባና እንደሚወጣ በደንብ ይወቁ፡፡ እራሰዎን ይህ ሰው ቢሮ ውስጥ ለምን መጣ ብለው ይጠይቁ፡፡ የማያውቁት ሰው ከሆነ ‹‹ ምን ልርዳዎት›› ብለው ይጠይቁ፡፡

የቢሮዎትን ቁልፍ፣ የመግቢያና የመውጫ መታወቂያዎን ፊት ለፊት አያስቀምጡ ወይም በቀላሉ ሊወሰዱ የሚችሉበት ቦታ ላይ አያስቀምጧቸው፡፡

በርና መስኮቶችን ይቆልፉ፡፡

አምሽተው በሚሰሩ ሰዓት ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ በሩን መቆለፍ፣ ለሰዎች የት እንዳሉ ማሳወቅ፣ ወደ መኪናዎ ወይም ወደ ታክሲ ወይም ባቡር በሰላም የሚሄዱበትን መንገድ መምረጥ፡፡

ለጽዳትና ለጥገና የሚመጡ ሰዎች መቼ እደሚመጡ ማወቅና መታወቂያቸውን ማረጋገጥ፡፡

አንድ የተሳሳተ ነገር ያለ መስሎ ከተሰማዎት ወዲያውኑ ለሚመለከተው ያመልክቱ፡፡

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home