የአሠሪና ሠራተኛ መብትና ግዴታ

Written by  Sunday, 25 October 2015 18:47
Rate this item
(30 votes)

የአሠሪና ሠራተኛ መብትና ግዴታ

                                                   ከ ማይ ዌጅM

My wage የተሰኘ የአለም ሥራ ድርጅት ILO አካል የሆነ ኢትዮጵያዊ ድርጅት  http://www.mywage.org/ethiopia/home በተሰኘ ዌብሳይቱ ስለ ሠራተኛው መብትና ግዴታ ያሠፈረውን ጵሁፍ ለተጠቃሚው ወገን ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች አስፍረነዋል፡፡

የደሞዝና የሥራ ቅኝት

ነፃ መከላከያ

የስራ ህጉ በተጨማሪም አሰሪዎች ለሰራተኞች የአደጋመከላከያ መሣሪያ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶች በማቅረብሰራተኞች ላይ ሊደርስ የሚችል የአደጋ እና የሌሎችበሠራተኞች  ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግርስጋቶችን ማስወገድ ይጠበቅበታል/አንቀፅ 92.3/

የአሰሪ ክብካቤዎች

 በስራ ህጉ አንቀፅ 92 መሠረት ማንኛውም ሰራተኛበስራ ቦታው አስፈላጊ ጥበቃዎችንና የደህነነትናየጤንነት ሁኔታዎችን የማግኘት መብት አለውአሰሪውም የሰራተኞችን ደህንነትና ጤንነት በሚገባለመጠበቅ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን መውሰድይጠበቅበታል፡

ስልጠና

አሰሪው ሰራተኞች የሚሰሩት ስራ ሊያስከትልባቸውስለሚችለው አደጋ እንዲሁም በጤንነት ላይ የሚደርስጉዳትን ለማስወገድ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄተገቢውን  ስልጠና እንዲሰጥ ይጠበቅበታል/አንቀፅ92.2/

ጤንነትና ደህንነትን የተመለከቱ ደንቦች

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ . 377/2003

ILO Convention 081.

የስራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎት

የስራ አዋጁ የስራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎትንበተመለከተ ድንጋጌዎች አሉት  /አንቀፅ 177-182/ነገር ግን አሁን ያለው አገልግሎት ከአለም አቀፍ የስራድርጅት ስምምነት 081 ጋር የተጣጣመ አይደለም

የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀፅ 61 መሰረት የመደበኛ የስራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት እና በሳምንት 48 ሰዓት ነው፡፡ የስራ ሰዓቶች በሳምንቱ የስራ ቀናት እኩል ይደለደላሉ፡፡
የስራው ፀባይ ቢያስገድድ ግን በማናቸውም የሣምንቱ የስራ ቀኖች ሰአቶችን ማሣጠርና ልዩነቱን ለተቀሩት ቀኖች ማደላደል ይቻላል፡፡ የስራ ሰዓታት በቀን እስከ10 ሰዓታት ማራዘም ይቻላል / አንቀፅ 63/ :: አንድ ሠራተኛ ትርፍ ሰዓት እንዲሰራ ሊገደድ ይችላል፡፡ ነገር ግን የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚሰራው ሠራተኛው ሌሎች እርምጃዎችን ይወስዳል ተብሎ በማይጠበቅበት ጊዜ፣ የደረሰ አደጋ ሲኖርና አደጋ ይደርሳል ተብሎ ሲገመት፣ ያልተጠበቁ ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ፣ አስቸኳይ ሥራ ሲኖርና ሳይቋረጥ መሠራት ባለበት ሥራ ላይ ሠራተኞች ከሥራ ሲቀሩ እነርሱን ለመተካት ሲባል ነው፡፡ትርፍ የስራ ሰዓታት በቀን 2 ሰዓት ወይም በወር 20 ሰዓት ወይም በዓመት 100 ሰዓት መብለጥ አይችልም ፡፡ 
አንድ ሠራተኛ በሳምንት ከተቀመጠው የስራ ሰዓት ማለትም በቀን 8 ሰዓት እና በሳምንት 48 ሰዓት በላይ ከሰራ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡- ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ መጠን 125% ከንጋቱ 12፡ዐዐ - ምሽቱ 4፡ዐዐ ሰዓት
-
ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ መጠን 15% ከምሽቱ 4፡ዐዐ ሰዓት - ንጋቱ 12፡ዐዐ ሰዓት
-
ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ መጠን 2ዐዐ% በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት
-
ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ክፍያ መጠን 25% በህዝባዊ በዓላት ቀን (አንቀፅ 61- 68)

መደበኛ ክፍያ

 በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀፅ 12 መሰረት አሰሪውለሠራተኛው ደመወዙንና ሌሎች ክፍያዎችን በዚህአዋጅ ወይም በህብረት ስምምነት መሠረት የመክፈልግዴታ አለበት፡፡ የደመወዝ ክፍያ የሚፈፀምበት ጊዜበህግ፣ በህብረት ስምምነት፣ በስራ ደንብ ወይም  በስራውል በተወሰነው መሰረት ይሆናል / አንቀፅ 58/

ስራና ደመወዝን የተመለከቱ ደንቦች

የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ . 377/2003

የምሽት ስራ ክፍያ

 በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ አንቀፅ 68 መሠረት የምሽትስራ ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት የሚሠራሥራ ማለት ነው፡፡ በሥራ ህጉ ላይ አሰሪዎቹ ለምሽትሠራተኞች ክፍያ  እንዲፈፅሙ የሚያደርግ አንቀፅየለም፡፡ ከፍተኛ ክፍያዎች የሚፈፀሙት የቀንሠራተኞች ሆነው በምሽት ትርፍ ስራ ለሚሰሩ ሰራተኞብቻ ነው፡፡ የምሽት ሰዓታት ትርፍ ሰዓታት ከሆኑለሠራተኛው የመደበኛውን ክፍያ 150% ማግኜትአለበት /አንቀፅ 68/

አነስተኛ የክፍያ ወለል

 ብሔራዊ የሆነ አነስተኛ የክፍያ  ወለል የለም፡፡ አነስተኛክፍያ ያለው በመንግስት ዘርፍ ብቻ ሲሆን ይህም 420ብር /24 የአሜሪካን ዶላር/ አካባቢ ነው ፡፡

 የህመም ፈቃድ ከክፍያ ጋር

የስራ ህጉ የህመም ፈቃድን ከክፍያ ጋር ይደነግጋል፡፡የህመም ፈቃዱ ከፍተኛው የጊዜ መጠን በአንድየካሌንደር አመት ውስጥ 6 ወራት ነው፡፡ ክፍያንበተመለከተም እንደሚከተለው ነው

. ለመጀመሪያው ወር ከሙሉ የደመወዝ ክፍያ ጋር

. ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ከደመወዙ ግማሽ ክፍያ ጋር

. ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ያለምንም ክፍያ /አንቀፅ85-86/

ስራና ህመምን የተመለከቱ ደንቦች

 የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ .377/2003

የማህበራዊ ጤና ዋስትና አዋጅቁጥ 690/2010

ህክምና

በህጉ ውስጥ ምንም የተደነገገ ነገር የለም፡፡ የማህበራዊጤንነት ዋስትና አዋጅ የሚል  አዲስ ህግ 2010ወጥቷል፡፡ ሁሉም ሰራተኞች የማህበራዊ ጤንነትዋስትና ዕቅድ  አባላት መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህህግ መሠረት አባላት የጤና አገልግሎቶች ያገኛሉ፡፡

በህመም ወቅት የስራ ዋስትና

 በህመም ፈቃድ ወቅት የሰራተኛው ስራ ዋስትናአለው፡፡

የአካል ጉዳት /የስራ ላይ ጉዳት ጥቅም

የስራ ላይ ጉዳቶች በአራት ይከፈላሉ / ዘለቄታዊ ሙሉመሰራት አለመቻል፣ / ዘለቄታዊ በከፊል መሰራትአለመቻል፣ / ጊዜያዊ መስራት አለመቻል እና /ሰራተኛውን ለሞት የሚበቃ አደገኛ ጉዳት

በዘለቴቃዊ መስራት አለመቻል/የአካል ጉዳት ወቅትበተገመገመው የሰራተኛው የጉዳት መጠን መሰረትከ47-70% ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ የጉዳትክፍያው ከእርጅና ጡረታው ካነሰ ወይም እኩል ከሆነከእርጅና ጡረታው ለሰራተኛው ይከፈለዋል፡፡ሰራተኛው የደረሰበት ጉዳት ቋሚና ለዘለቄታውምየማያሰራው ከሆነ የዓመታዊ ደመወዝ አምስት እጥፍበአንድ ጊዜ ይከፈለዋል፡፡ /የአምስት አመት ደመወዝ/፡፡

በጊዜያዊ ጉዳት ወቅት የሰራተኛው መሠረታዊ ደመወዝ47% 5 /ዓመት/ ተባዝቶ ይህም በተገመገመውየጉዳት መጠን ተባዝቶ እንደ ጊዜያዊ የጉዳት ጥቅምይከፈለዋል፡፡

 ለሞት በሚያበቃ ጉዳት ወቅት ጥገኞች /ባል/ሚስት፣ከ18 ዓመት በታች ያሉ ህፃናትና ህይወቱ ባለፈውሰራተኛ ይደገፉ የነበሩ ወላጆች/ ጡረታ ያገኛሉ፡፡ህይወቱ ያለፈው  ሰራተኛ ሊያገኘው ይችል ከነበረውጡረታ 50% የተገመገመው ዘለቂታው ሙሉ  ጉዳትከሆነ ለባል/ሚሰት ይከፈላል፡፡ እድሜያቸው 15በታች ለሆኑ የሟች ልጆች ለእያንዳንዱ 10%፣በሟችሠራተኛ ድጋፍ ይረዱ ለነበረ የሟች ወላጆችለእያንዳንዳቸው አስር በመቶ በአንድ ጊዜ በአሰሪውይከፈላላ / አንቀጽ 95-112 የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይአዋጅ

የማህበር አባል የመሆን ነፃነት

ህገመንግስቱም ሆነ የሰራተኛ ህጉ የመደራጀት ነፃነትንየሚፈቅዱ ሲሆን ሰራተኞችና አሰሪዎችም ማህበርመመስረት እንደሚችሉ ይደነግጋሉ፡፡ ይህ መብት በህግአግባብ የሚተገበር ይሆናል /የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅከአንቀፅ 113 ጀምሮ እና የህገ መንግስቱ አንቀፅ 42.1

በህብረት የመደራደር ነፃነት

የስራ ህጉ በህብረት መደራደርን ዕውቅና ሰጥቶታል /ከአንቀፅ 124 ጀምሮ/

የሰራተኛ ማህበራትን የተመለከቱ ደንቦች

Social Health Insurance Proclamation No.690/2010;

Private Organization Employees Pension Proclamation No. 715/2011;

Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, 1995.

ስራ የማቆም መብት

 ስራ የማቆም መብት በህገ መንግስቱ ተደንግጓል /አንቀፅ 42.1. በስራ ህጉም  /አንቀፅ 157-160/ የህግአግባብ ተበጅቶለታል/ ቢሆንም ግን በስራ የማቆምመብት ላይ የሚደረጉ ምክንያታዊ ያልሆኑ እገዳዎች /ረጅም የአስፈላጊ አገልግሎቶች ዝርዝር፣ 

ባልተፈቀዱ የስራ ማቆም እርምጃዎች ላይ በተሳተፉሰዎች ላይ የሚጣሉ ተመጣጣኝ ያልሆኑ የወንጀልናየፍትሀብሔር እገዳዎች እና የተንዛዙ ሂደቶች/ ይህንንመብት ያኮላሹታል፡፡  

ህፃናት ልጆችና ሌሎች የቤተሰብ ሀላፊነት ላሉባቸው ሠራተኞች የሚበጁ አማራጭ

በህጉ ውስጥ የወላጆች እና የቤተሰብ ሀላፊነት ያለባቸውሰራተኞች የስራና ህይወት ሚዛን ይጠብቁ ዘንድ አጋዥየሆኑ ድንጋጌዎች የሉም፡፡

የወላጅነት ፈቃድ

የወሊድ ፈቃድ ካበቃ በኋላ ስለሚኖር የወላጅነት ፈቃድምንም ድንጋጌ የለም

ወሊድ እና ሥራን የተመለከቱ ድንጋጌዎች

የአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 377/2003 

የወሊድ ፈቃድ

ሴት ሰራተኞች 90 ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከውሉ ክፍያጋር የማግኘት መብት አላት:: ይህም ከመውለዷ በፊት30 ቀናት እንዲሁም ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት

 ይሆናል /አንቀፅ 88/

የአባትነት ፈቃድ

በሠራተኛ ሕግ 2003 ውስጥ የአባትነት ፈቃድን የተመለከተ ምንም ዓይነት ድንጋጌ የለም፡፡ ነገር ግን አንቀጽ 81 ለልዩና አደገኛ ሁኔታዎች እስከ 5 ተከታታይ ቀናት ያለክፍያ እረፍት ይፈቅዳል፡፡

ከክፍያ ጋር ዕረፍት/ አመታዊ ፈቃድ

ሰራተኞች ለመጀመሪያ የአንድ አመት አገልግሎት 14የስራ ቀናት ከክፍያ ጋር  እንዲሁም ከአንድ አመት በላይለሆነ አልግሎት ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎትዓመት አንድ የስራ ቀን ዕረፍት የማግኘት መብትአላቸው /አንቀጽ 77/  የአምስት ዓመት አልግሎትያለው ሰራተኛ  18 የሥራ ቀናት ከክፍያ ጋር ዕረፍትይኖረዋል፡፡

ስራና በዓላትን የተመለከቱ ደንቦች

 የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ . 377/2003

በህዝባዊ በዓላት ወቅት ክፍያ

ሰራተኞች በበዓላት /ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ/ ወቅትከክፍያ ጋር ዕረፍት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህምመታሰቢያ እና ሀይማኖታዊ /ክርስቲያንና ሙስሊም/በዓላትን  ይጨምራል፡፡ እነዚህም በቁጥር 13 ናቸው፡፡/ የህዝባዊ በዓላት እና የእረፍት ቀናት አዋጅ 1975

 1996 እንደተሻሻለው  የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅአንቀፅ 73-75/

የሳምንት መጨረሻ / የህዝባዊ በዓላት ስራ ክፍያ

በህዝባዊ በዓላት ቀናት የሚሰራ ስራ ክፍያ አለው፡፡አንድ ሰራተኛ በህዝባዊ በዓላት

ቀናት ስራ ከሰራ የመደበኛውን ክፍያ 200% ክፍያያገኛል /አንቀፅ 75/

Compensatory Holidays/rest days

 አንድ ሰራተኛ በምትክ የሚሰጥ የዕረፍት ጊዜ ሳይወስድየስራ ውሉ ቢቋረጥ በሠራው ሰዓት መጠን የማካካሻገንዘብ ይሰጠዋል/አንቀፅ 71/፡፡ በህዝባዊ በዓላት ቀናትለሚሰሩ ሰራተኞች የሚሰጥ የምትክ ዕረፍት ጊዜንየተመለከተ ድንጋጌ የለም፡፡

ሳምንታዊ የዕረፍት ቀን

 ሰራተኞች በሳምንት ለአንድ ቀን /24 ተከታታይሰዓታት/ የማረፍ መብት አላቸው:: ይህም ዕሁድ ቀንይውላል /አንቀፅ 69/ ፡፡ 

የተወሰነ ጊዜ ውል

የኢትዮጵያ አሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የቋሚነት ባህርይላላቸው ስራዎች የውስን ጊዜ

 ሰራተኞች መቅጠርን ይከለክላል፡፡

በፅሁፍ የተቀመጡ የቅጥር ጉዳዮች

የግለሰብ የቅጥር ስምምነት በቃል ወይም በፅሁፍ ሊሆንይችላል፡፡ ማንኛውም ሰው የተወሰነ ስራ ለአሰሪውለመስራት ቢስማማ በሁለቱ መካከል የስራ ውልይመሠረታል፡፡ የስራ ውል በፅሁፍ ያልተደረገ ከሆነየቃሉ ውል በተደረገ 15 ቀናት ውስጥ የተዘረዘሩሁኔታዎችን የያዘ ፅሁፍ መግለጫ ለሠራተኛው መስጠትይጠበቅበታል፡፡ /አንቀፅ 04-10/

የሙከራ ጊዜ

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሠረት የሙከራ ጊዜ አንድሰው በስራ ውሉ መሠረት ሊመደብበት ለታቀደው ቦታተስማሚ መሆኑን ለመመዘን የሚደረግ ነው፡፡ የሙከራጊዜው ስምምነት በፅሁፍ መደረግ ሲኖርበት 45ተከታታይ ቀናት ሊበልጥ አይችልም፡፡ /አንቀጽ 11/ 

የስራ ሁኔታዎችን የተመለከቱ ደንቦች

የአሰሪና ሰራተኛ ዓዋጅ . 377/2003

የማስታወቂያ አስፈላጊነት

ማንኛውም ወገን ማስታወቂያ በመስጠት ወይምአስፈላጊውን ክፍያ  በመፈፀም ውሉን ሊያቋርጥይችላል፡፡ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ መሰረት የስራ ውልከሰራተኛው ጠባይ ወይም የሠራተኛውን የመስራትችሎታ ወይም ከድርጅቱ ድርጅታዊ አቋም ወይም የስራእንቅስቃሴ ጋር ባላቸው ምክንያቶች ሊቋረጥ ይችላል፡፡/አንቀጽ 26/ አዋጁ በተጨማም የስራ ውልያለማስጠንቀቂያ ሊቋረጥ የሚችልባቸውን ሁኔታዎችይጠቅሳል /አንቀፅ 27/ ውሉን ማቋረጥ የፈለገ ሰራተኛለአሰሪው 30 ቀናት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥይችላላ፡፡ /አንቀጽ 31/ በሌላ በኩል አሰሪውከሰራተኛው ጋር ያለውን የስራ ውል ማቋረጥ ከፈለገማስታወቂያ የሚሰጠው በሚከተለው መሰረት ነው፡፡>የሙከራ ጊዜያቸውን ለጨረሱና የአገልግሎትጊዚያቸው ከአንድ አመት ላልበለጠ አንድ ወር,  ከአንድእስከ ዘጠኝ /1-9/ ዓመት የአገልግሎት ጊዜ ላላቸውሁለት ወራት, 9 አመት በላይ አገልግሎት ጊዜ ላላቸውሶስት ወራት, የሙከራ ጊዜያቸውን ለጨረሱ ግንየሰራተኛ ቅነሳ በማስፈለጉ ምክንያት ውላቸውለሚቋረጥ ሰራተኞች ሁለት ወራት /አንቀፅ 35/

የስራ ስንብት ክፍያ

አሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አንቀፅ 39-40 መሰረት የስራስንብት ክፍያ/ የሙከራ ጊዜውን ለጨረሰ/ ለሠራተኛየሚከፈለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፡፡ ድርጅቱበመክሰሩ ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱየሥራ ውሉ ሲቋረጥ ሰራተኛው ከስራ ሲቀነስአሰሪው ከህግ አግባብ ውጭ የሆነና የሠራተኛውንመብት የሚጎዳ ነገር ሲፈፅም አሰሪው ለሰራተኛውደህንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋ አደጋ እንዳይደርስማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ዕርምጃ ሳይወሰድ ሲቀር እና በሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት ምክንያት የስራ ውሉሲቋረጥ 

 የስራ ስንብት ክፍያው መጠን በአገልግሎት ዘመንላይም የተመሰረተ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ለአንድአመት አገልግሎት 30 ቀናት ደመወዝ /ከአንድ አመትበታች ላገለገሉሠራተኞች የስራ ስንብት ክፍያውባገለገሉበት ጊዜ መጠን ተሰልቶ ይከፈላቸዋል/; 30ቀናት ደመወዝና ለእያንዳንዱ ተጨማሪ አመት 10ቀናት ክፍያ / የስራ ስንብት ክፍያ ከሁለት ወራትደመወዝ አይበልጥም/; የስራ ውላቸው በቅነሳ ምክንያትለሚቋረጥ ሰራተኞች ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪየ60 ቀናት ደመወዝ ይከፈላቸዋል /አንቀፅ 40/

የጡረታ መብቶች

ህጉ ሙሉ እና ከፊል ጡረታን ይደነግጋል፡፡ ለሙሉጡረታ ሰራተኛው 60 ዓመት  የሞላው /ለሴቶችምተመሳሳይ ነው/ እና 120 ወራት / 10 ዓመታት/አልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ አስቀድሞ ጡረታመውጣትም የሚቻል ሲሆን ለዚህም ሰራተኛው 55ዓመት የሞላውና ቢያንስ 300 ወራት /25 ዓመታት/አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ የዕርጅና ጡረታመጠን ሰራተኛው ባለፉት ሶስት አመታት   ውስጥያገኘው የነበረው አማካይ ወርሃዊ ደመወዝ 30% ሆኖበዚህ ላይም ዋስትና ያለው  ሰራተኛ 10 ዓመት በላይለፈፀመው ለእያንዳንዱ ዓመት አገልግሎት አማካይወርሃዊ ደመወዝ 1.25% በመደመር ይታሰባል፡፡

የስራ አጥነት ጥቅም

በኢትዮጵያ የሰራተኛ ህጐች ውስጥ የስራ አጥነትጥቅምን የተመለከቱ ድንጋጌዎች የሉም

የጥገኞች ተተኪዎች ጥቅም

ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በህይወት ላሉ ጥገኞች ባል/ሚስት ህፃናት እና ወላጆች  በህይወት ያለ የትዳር ጓደኛወይም ህፃናት ከሌሉ ጥቅሞችን ይደነግጋሉ፡፡ ይህምየሟቹ ጡረታ 50% ሲሆን ይህም ለባል/ሚስትይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 20% ለእያንዳንዱ ወላጅየሞተበት ህፃን ይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 30%ለእያንዳንዱ ሁለቱም ወላጅ ለሞተበት ህፃንይከፈላል፡፡ የሟቹ ጡረታ 15% ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወላጅ ይከፈላል፡፡ አግባብነት ያላቸው በህይወት ያሉሰዎች ከሌሉ ጥቅሙ የሟቹ ጡረታ 20% ይሆናል፡፡

ማህበራዊ ዋስትናን የተመለከቱ ደንቦች

የማህበራዊ ጤና ዋስትና አዋጅ ቁጥ 690/2010

የግል ድርጅት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ  715/2011የመስራት አለመቻል / ጥቅሞች

ከላይ የተጠቀሱት ህጐች በዘለቄታነት መስራትየማያስችሉ ከስራ ጋር ግንኙነት የሌላቸው አደጋዎች /ጉዳዮች/ በሽታዎችን የተመለከቱ ድንጋጌዎችአሏቸው፡፡ ሰራተኛው መደበኛ ጥቅም የሚያስገኝ ስራመስራት የማያስችል የተገመገመ ችግር  ያጋጠመውናየ10 ዓመት አገልግሎት ያለው መሆን አለበት፡፡ስሌቱም የሚሰራው ከእርጅና ጡረታ ጋር በተመሣሣይነው፡፡ መስራት ያለመቻል ጡረታ ሰራተኛው ከጉዳቱበፊት ባሉት ሶስት አመታት የነበረው ወርሃዊ ገቢ 30%በዚህ ላይም ዋስትና ያለው ሰራተኛ 10 ዓመታትበላይ ላበረከተው አገልግሎት የአማካይ ወርሃዊ ገቢ1.25% በመደመር ይሆናል፡፡

የወሊድ ፈቃድ

ሴት ሰራተኞች 90 ቀናት የወሊድ ፈቃድ ከውሉ ክፍያጋር የማግኘት መብት አላት:: ይህም ከመውለዷ በፊት30 ቀናት እንዲሁም ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት

 ይሆናል /አንቀፅ 88/

ጎጂ ሥራዎች

(Art. 87) የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ሴቶች ከባድ ወይምለጤናቸው ጎጂ ናቸው ተብለው ሚኒስቴሩበሚዘረዝራቸው ሥራዎች ላይ ማሰማራትን /ነፍሰጡሮች ቢሆኑም  ባይሆኑም/ ይከለክላል፡፡በተመሣሣይም ነፍሰ ጡር ሰራተኞች ትርፍ ሰዓትወይም የምሽት ስራዎችን እንዲሰሩ አይጠየቁም፡፡ነፍሰጡር የሆነች ሰራተኛ የምትሰራው ስራ ለራሷጤንነትም ሆነ ለፅንሷ አደገኛ ከሆነ ወደ ሌላ የስራ ቦታተመድባ መስራት አለባት/አንቀፅ 87/ 

ለሰራተኛ ሴቶች የማጥባት ዕረፍት

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አሰሪዎች ለሚያጠቡ እናቶችእረፍት እንዲሰጥ የሚጠይቅ

 ድንጋጌ የለውም

ነፃ የህክምና አገልግሎት

በወሊድ ህክምናን በተመለከተ ምንም አይነት ድንጋጌየለም፡፡ እኤአ 2010 አዲስ የማህበራዊ 

ጤና ደንብ አዋጅ ወጥቷል፡፡ ይህም ሁሉም ሠራተኞችየማህበራዊ ጤና መድን ዕቅድ አባላት እንዲሆኑይጠይቃል፡፡ ቢሆንም ይህ ህግ ወሊድን የተመለከቱየጤንነት ጥቅሞችን በቀጥታ አይመለከትም፡፡

ወሊድ እና ሥራን የተመለከቱ ድንጋጌዎች

 የአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 377/2003 

Constitution of Ethiopia, 1995.

ገቢ

 የወሊድ ፈቃድ ከሙሉ ክፍያ ጋር የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡የስራ ህጉ ነፍሰ ጡር ሰራተኛ በመጀመሪያው 30 የፈቃድቀናት ሙሉ ክፍያ ይሰጣታል የሚል ሲሆን ከወሊድበኋላ ስላሉት 60 ቀናት የሚለው ነገር የለም፡፡ ነገር ግንህገ መንግስቱ በአንቀፅ 35.5. መሰረት ሴት ሰራተኞችየወሊድ ፈቃድ ከመሉ ክፍያ ጋር የማግኘት መብትእንዳላቸው ይደነግጋል፡፡

ከስራ ከመባረር ጥበቃ

ማንኛውም አሰሪ ሴት ሰራተኛ ነፍሰጡር በሆነችበትጊዜና ከወለደችበት ቀን ጀምሮ በአራት ወራት ጊዜውስጥ ከስራ ሊያሰናብት አይችልም፡፡ ነገር ግን ሴትሰራተኛ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር ባልተያያዙምክንያቶች ልትሰናበት ትችላለች / የአሰሪና ሰራተኛአዋጅ አንቀፅ 87.5/ 

ነፃ መከላከያ

የስራ ህጉ በተጨማሪም አሰሪዎች ለሰራተኞች የአደጋመከላከያ መሣሪያ ልብስና ሌሎች ቁሳቁሶች በማቅረብሰራተኞች ላይ ሊደርስ የሚችል የአደጋ እና የሌሎችበሠራተኞች  ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የጤና ችግርስጋቶችን ማስወገድ ይጠበቅበታል/አንቀፅ 92.3/

የአሰሪ ክብካቤዎች

 በስራ ህጉ አንቀፅ 92 መሠረት ማንኛውም ሰራተኛበስራ ቦታው አስፈላጊ ጥበቃዎችንና የደህነነትናየጤንነት ሁኔታዎችን የማግኘት መብት አለውአሰሪውም የሰራተኞችን ደህንነትና ጤንነት በሚገባለመጠበቅ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን መውሰድይጠበቅበታል፡

ስልጠና

አሰሪው ሰራተኞች የሚሰሩት ስራ ሊያስከትልባቸውስለሚችለው አደጋ እንዲሁም በጤንነት ላይ የሚደርስጉዳትን ለማስወገድ ስለሚያስፈልገው ጥንቃቄተገቢውን  ስልጠና እንዲሰጥ ይጠበቅበታል/አንቀፅ92.2/

ጤንነትና ደህንነትን የተመለከቱ ደንቦች

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ . 377/2003

ILO Convention 081.

የስራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎት

የስራ አዋጁ የስራ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አገልግሎትንበተመለከተ ድንጋጌዎች አሉት  /አንቀፅ 177-182/ነገር ግን አሁን ያለው አገልግሎት ከአለም አቀፍ የስራድርጅት ስምምነት 081 ጋር የተጣጣመ አይደለም

የመስራት መብት

ሴቶች ከወንዶች ጋር በተመሣሣይ በተለይምለጤናቸው ጎጂ በሆኑ ስራዎች ላይ አይሰማሩም

የግዳጅ ስራ

የግዳጅ ስራ በህገ መንግስቱ የተከለከለ ነው / አንቀፅ18.2እና 18.3/

ስራን የመቀየር ነፃነት እና ስራን የመተው መብት

ሰራተኞች ለአሰሪያቸው ማስታወቂያ ከሰጡ በኋላስራቸውን የመቀየር መብት አላቸው::

ዕኩልነት

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 25 መሠረት ሁሉምሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው በመካከላቸውምበዘር፣በብሔር፣ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በጾታ፣በቋንቋ፣በሀይማኖት፣በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነትአይደረግባቸውም ፡፡ የአካል ጉዳተኛ ስዎችን የመቀጠርመብት አዋጁም በአካል ጉዳት  ምክንያት የሚደረግየቅጥር ልዩነትን ይከለክላል፡፡

ህፃናት በስራ ቦታ

አነስተኛው የስራ ዕድሜ 14 ዓመት ነው / የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀፅ 89.2/ አደገኛ ሥራ ላይ የመሳተፍ አነስተኛው ዕድሜ 18 ነው፡፡ ዕድሜአቸው 14-18 ዓመት የሆኑ ሠራተኞች ወጣት ሠራተኞች ይባላሉ፡፡ የሥራው ተፈጥሮ ወይም አሠራሩ ሕይወታቸውን ወይም ጤንነታቸውን አደጋ ላይ ሊጥል በሚችል ሥራ ላይ ወጣት ሠራተኞችን መቅጠር የተከለከለ ነው፡፡ የተከለከሉ የሥራ ዓይነቶችን ዝርዝር የሚኒስቴር /ቤቱ የሚወስን ሲሆን ከሚያካትታቸው መካከል፡- መንገደኞችና ቁሳቁስን ማጓጓዝ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮች ላይ መስራት፣ የምድር ውስጥ ማዕድን ቁፋሮ የከበሩ ድንጋዮች መሰብሰብ፣ በፍሳሽና በቱቦ ቁፋሮ መስራት ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን የሠራተኛ ሕጉ 14 ዓመት በላይ ያሉ ወጣቶች በመንግስት ተቀባይነት ያገኙ የሙያ ስልጠና ኮርሶችን ከወሰዱ በኋላ በአደገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል፡፡ መንግስት የወጣት ሠራተኞች መመሪያን ያወጣ ሲሆን መመሪያው በውስጡ አደገኛ ሥራዎችን በተመለከተ የተሻሻለ ዝርዝር ይዟል፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት መካከል በማዕድን ማውጫ ሥፍራዎች፣ በመስታወት ፋብሪካዎች፣ የቤት ውስጥ እና በመንገድ ላይ መስራት ይገኙበታል፡፡ የወጣት ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን ከሰባት ሰዓት መብለጥ አይችልም፡፡ ወጣት ሠራተኞችን ከምሽቱ 400 ሰዓት እስከ ንጋቱ 1200 ሰዓት ድረስ፣ ትርፍ ሰዓት፣ በሳምንት የእረፍት ቀናቸው፣ በበዓላት ቀን ቀጥሮ ማሰራት የተከለከለ ነው፡፡ (የሠራተኛ ሕግ አንቀጽ 89-91)

የስራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ

የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከለክልሲሆን 18 - 24 ወራት

 እስራትን ይደነግጋል፡፡

በስራ ቦታ ፍትሀዊ አያያዝን የተመለከቱ ደንቦች

Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, 1995

The Criminal Code Proclamation No. 414/2004

አዋጅ . 377/2003

የመስራት መብት

ሴቶች ከወንዶች ጋር በተመሣሣይ በተለይምለጤናቸው ጎጂ በሆኑ ስራዎች ላይ አይሰማሩም

የግዳጅ ስራ

የግዳጅ ስራ በህገ መንግስቱ የተከለከለ ነው / አንቀፅ18.2እና 18.3/

ስራን የመቀየር ነፃነት እና ስራን የመተው መብት

ሰራተኞች ለአሰሪያቸው ማስታወቂያ ከሰጡ በኋላስራቸውን የመቀየር መብት አላቸው::

ዕኩልነት

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 25 መሠረት ሁሉምሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው በመካከላቸውምበዘር፣በብሔር፣ብሔረሰብ፣ በቀለም፣ በጾታ፣በቋንቋ፣በሀይማኖት፣በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነትአይደረግባቸውም ፡፡ የአካል ጉዳተኛ ስዎችን የመቀጠርመብት አዋጁም በአካል ጉዳት  ምክንያት የሚደረግየቅጥር ልዩነትን ይከለክላል፡፡

ህፃናት በስራ ቦታ

አነስተኛው የስራ ዕድሜ 14 ዓመት ነው / የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀፅ 89.2/ አደገኛ ሥራ ላይ የመሳተፍ አነስተኛው ዕድሜ 18 ነው፡፡ ዕድሜአቸው 14-18 ዓመት የሆኑ ሠራተኞች ወጣት ሠራተኞች ይባላሉ፡፡ የሥራው ተፈጥሮ ወይም አሠራሩ ሕይወታቸውን ወይም ጤንነታቸውን አደጋ ላይ ሊጥል በሚችል ሥራ ላይ ወጣት ሠራተኞችን መቅጠር የተከለከለ ነው፡፡ የተከለከሉ የሥራ ዓይነቶችን ዝርዝር የሚኒስቴር /ቤቱ የሚወስን ሲሆን ከሚያካትታቸው መካከል፡- መንገደኞችና ቁሳቁስን ማጓጓዝ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮች ላይ መስራት፣ የምድር ውስጥ ማዕድን ቁፋሮ የከበሩ ድንጋዮች መሰብሰብ፣ በፍሳሽና በቱቦ ቁፋሮ መስራት ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን የሠራተኛ ሕጉ 14 ዓመት በላይ ያሉ ወጣቶች በመንግስት ተቀባይነት ያገኙ የሙያ ስልጠና ኮርሶችን ከወሰዱ በኋላ በአደገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል፡፡ መንግስት የወጣት ሠራተኞች መመሪያን ያወጣ ሲሆን መመሪያው በውስጡ አደገኛ ሥራዎችን በተመለከተ የተሻሻለ ዝርዝር ይዟል፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት መካከል በማዕድን ማውጫ ሥፍራዎች፣ በመስታወት ፋብሪካዎች፣ የቤት ውስጥ እና በመንገድ ላይ መስራት ይገኙበታል፡፡ የወጣት ሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን ከሰባት ሰዓት መብለጥ አይችልም፡፡ ወጣት ሠራተኞችን ከምሽቱ 400 ሰዓት እስከ ንጋቱ 1200 ሰዓት ድረስ፣ ትርፍ ሰዓት፣ በሳምንት የእረፍት ቀናቸው፣ በበዓላት ቀን ቀጥሮ ማሰራት የተከለከለ ነው፡፡ (የሠራተኛ ሕግ አንቀጽ 89-91)

የስራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ

የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከለክልሲሆን 18 - 24 ወራት

 እስራትን ይደነግጋል፡፡

በስራ ቦታ ፍትሀዊ አያያዝን የተመለከቱ ደንቦች

Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, 1995

The Criminal Code Proclamation No. 414/2004

 

አዋጅ . 377/2003

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Workplace safety የአሠሪና ሠራተኛ መብትና ግዴታ