Print this page

የመንገድ ደህንነት ለልጆች

Written by  Thursday, 29 October 2015 17:12
Rate this item
(0 votes)
  • 0 Comments

የመንገድ ደህንነት ለልጆች

 

ይህ የልጆች መንገድ ደህንነት ተብራርቶ የቀረበው ለወላጆችና ለልጆች ነው፡፡ ልጆች መንገድ ላይ ደህንነታቸው እንዲተጠበቅ ያደርጋል፡፡

ልጆች ያዩትን ነገር ለሞመከር ወይም ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው፡፡ ስለሆነም ወላጆች ጥሩ ምሳሌ መሆን አለባቸው ለልጆቻቸውም የመንገድ ደህንነት በጊዜ መጀመር አለባቸው፡፡

የመንገድ ደህንነት በሁሉም እድሜ ማስተማር ጠቃሚ ነው፡፡ ልጆች በሚያድጉ ጊዜ በግላቸው ውሳኔ መወሰንና በተሳሳተ መልኩ ሁሉንም ነገር እንደሚያውቁ ያምናሉ፡፡ ስለሆነም የመንገድ ደህንነት በቀላሉ መታየት የሌለበት ጉዳይ እንደሆነና ህጉንም መጣስ እንደማይቻል በጥብቅ ማወቅ አለባቸው፡፡

ልጆች የተለየ አመለካከት ይፈልጋሉ ምክንያቱም፡-

ልጆች በተፈጥሮ ደፋሮችና አንድን ነገር ለመሞከር ፈጣኖች ስለሆኑ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ከልጆች ጋር ተያያዥነት ያላቸው አደጋዎች የሚያጋጥሙት ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ነው፡፡

ለአደጋ ተጋላጭነታቸው የሚጨምረው ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ ነው፡፡

ምን መጠንቀቅና ምን መስማት እንዳለባቸው አያውቁም፡፡

ነፃነትን ማጣጣም ይፈልጋሉ፡፡

ፈጣኖችና የማይጨበጡ ናቸው፡፡

በቀላሉ ሃሳባቸው ይሰረቃል፡፡

የነፃነት መንገዶች

ልጆችን በሚገባቸው ቋንቋ ማውራት፡፡

የመንገድ ደህንነት የትራፊክ ፍሰቱ አነስተኛ በሆነ መንገድ ላይ አስተምሯቸው፡፡

ብቻቸውን እንዲሻገሩ ከመፍቀድዎ በፊት መጀመሪያ ይፈትንዋቸው፡፡

የትራፊክ ፍሰት ያላቸው መንገዶች ላይ ከልጆችዎ ጋር አብረው መሻገር፡፡ ይህንንም ደጋግሞ ማድረግ፡፡

በመንገዱ ላይ በህገወጥ መንገድ የሚያሽከረክሩትን እየለዩ ምን ዓይነት ጥፋት እየሰሩ እንደሆነና ጥፋቱ እንዴት እንደሚስተካከል ለልጆችዎ ማሳየት፡፡

ልጆችዎ ብቻቸውን እንዲጓዙ ከመፍቀድዎ በፊት ችግር ቢፈጠር እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ማሳወቅ፡

ከወላጆች ወይም ከአዋቂዎች የሚጠበቅ፡-

ልጆችዎን በማንኛውም የትራፊክ እንቅስቃሴ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሳየት፡፡

እውቀታቸውና ችሎታቸውን ተጠቅመው አደገኛ የሆኑ ክስተቶችን በንቃት እንዲከታተሉ ማድረግ፡፡

የልጆችዎን ደህንነት ለመጠበቅ በመንገድ ሲጓዙ እጃቸውን መያዝ፣ በመኪና ውስጥ ቀበቶ ማሰር፣ ብስክሌት ሲነዱ ደግሞ የአደጋ መከላከያ ኮፍያቸውን እንዲያደርጉ ማሳሰብ፡፡

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ መንገድ ደህንነት ማሳወቅ፡፡

ስለ ደህንነት ማውራት ብቻ ሳይሆን በደህንነት ላይ ያላቸውንም ንቃት መከታተል፡፡

ከሁሉም በላይ በልጆችዎ አይተማመኑ

አዋቂዎች በልጆች ደህንነት ኃላፊነት አለብን የእግር መንገድ ሲሄዱ፣ ብስክሌት ሲነዱ፣ ሲጫወቱና በመኪና ሲሄዱ

ለልጆች

መጀመሪያ የምትሄዱበትን አቅዱ

ወዴት እንደምትሄዱ እርግጠኛ ሁኑ

ጥሩ የሆነውን መንገድ ምረጡ

ለራሳችሁ ሰፊ ጊዜ ስጡ

በእግር በምትጓዙ ጊዜ

በእግረኛ መሄጃ ብቻ ተጓዙ፡፡

የእግር መሄጃ ምልክት ከሌለ ቀኛችሁን ይዛችሁ ተጓዙ ምክንያቱም ወደ እናንተ የሚመጡትን መኪኖች ማየት እንድትችሉ፡፡

ከሁለት በላይ ከሆናችሁ መጠምዘዣ ቦታ ላይ እና የትራፊክ መጨናነቅ ባለበት ቦታ ላይ ከፊትና ከኋላ ሁኑ፡፡

ከሩቅ መንገዱ ካልታያችሁ በጥንቃቄ ተጓዙ፡፡

ብስክሌት፣ መኪና የመሳሰሉትን ስትሻገሩ ተጠንቀቁ ምክንያቱም በቀስታ እየተጓዙ ቢሆን እንኳ ሙሉ በሙሉ ሊያስቆማቸው የሚችል ፍሬን ስለማይኖራቸው አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉና፡፡

ከታናናሾቻችሁ ጋር እየተጓዛችሁ ከሆነ በምትሻገሩ ሰዓት እጃቸውን ያዝዋቸው፡፡

በመኪና መንገድ ሳይሆን በእግረኛ መንገድ መሃሉን ይዛችሁ በቀጥታ ተጓዙ፡    ምክንያቱም ኣንዳንዲ በድንገት የመኪና በር ሊከፈት ስለሚችል በሩ ሊመታችሁ ይችላል፡፡

በመጫወቻ ቦታ እንደምትጫወቱት ዓይነት በመኪና መንገድ ላይ እንዳታደርጉ፡፡

ጓደኞቻችሁ በሌላኛው መንገድ ሆነው ቢጠርዋችሁ ሳትጣደፉ መኪና አይታችሁ ተሻገሩ፡፡

ጓደኞቻቹህን ለአደጋ የሚያጋልጥ ነገር እንዲያደርጉ አታበረታቷቸው፡፡

የእግር ጉዞ በምሽት

አሽከርካሪዎች እንዲያይዋቹ ምንግዜም ነጣ ያለ ልብስ ልበሱ፡፡

በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ አትውጡ፡፡

ቀለማቸው የሚንያንፀባርቅ መሳርያዎች ጥሩ ናቸው ምክንያቱም በቀንም በጨለማም ስለሚታዩ፡፡

 

የመኪና መንገድን እንዴት በሰላም እንደምንሻገር

መጀመሪያ አስበው - ያቅዱ

ለመሻገር የሚመች ሁነኛ ቦታ መርጠው ይቁሙ፡፡

የዜብራ መሻገሪያ፣ የትራፊክ መብራት፣ ትራፊክ ባለበት መኪኖች ሲቆሙ እግረኛ በሚሻገርበት ሰዓት መሻገር፡፡

በመንገዱ ላይ  የዜብራ መሻገሪያ፣ የትራፊክ መብራት፣ ትራፊክ ከሌለ ግን በሁሉም አቅጣጫ መንገዱን ማየት የሚችሉበትና አሽከርካሪዎችም እርስዎን ማየት የሚቻላቸው ቦታ መርጠው ይሻገሩ፡፡

መጠምዘዣ ቦታዎች ላይ አይሻገሩ፡፡

ቁም

ከመኪኖች ራቅ  ብላችሁ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ በሚያሻግረው ቦታ ላይ ቁሙ ፡ ግን መንገዱን ሁሉ ማየት የሚችሉበት ቦታ ይሁን ከመኪና ራቅ ያለ መቆምያ ባይኖርም፡፡

አይቸኩሉ ለራስዎ ጊዜ ሰጥተው በደንብ አይተው ይሻገሩ፡፡

አይተው ያዳምጡ

የትራፊክ ፍሰቱን በሁሉም አቅጣጫ ተመልከተው ያዳምጡ፡፡

ለመሻገር እስከሚቻል ድረስ ጠብቁ

በትእግስት መኪኖቹ እስከሚያልፉ ጠብቁ፡፡

ሰፋ ያለ የመሻገሪያ ክፍተት ሲያገኙና በቂ የመሻገሪያ ሰዓት እንዳለዎት ሲያውቁ  ይሻገሩ፡፡

እርግጠኛ ካልሆኑ ግን እንዳይሻገሩ፡፡

በደንብ አይተው ይሻገሩ

ለመሻገር እደሚችሉ ካረጋገጡ በኋላ ይሻገሩ፡፡

በመሻገር ላይ ባሉበት ሰዓትም በደንብ እያዩና እያዳመጡ ይሻገሩ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ሲሻገሩ እንዳይሮጡ፡

 

የቆሙ መኪኖች ባሉበት መሻገር

በቆሙ መኪኖች መካከል አይሻገሩ፡፡

አማራጭ ከሌሎት ግን፡-

በሁለት የቆሙ መኪኖች መካከል በቂ የማለፍያ ቦታ እንዳለ ያረጋግጡ፡፡

ለመውጣት የተዘጋጀ መኪና አለመኖሩን ማየት መኪና ውስጥ ሹሬሩ መኖሩንና መብራት መብራቱን፡  ከዚያም የሞተር ድምጽ መኖሩን ማዳመጥ፡፡ ከኣሽከርካሪው ጋር ለመተያየት መሞከር፡ 

በቀላሉ ወደ ሌላኛው መንገድ መሻገር እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን፡፡

መኪኖች የቆሙበትን ቦታ እንደጨረሱ ይቁሙ፡፡

በቀኝም በግራም መኪና እንደሌለ ይመልከቱ፡፡

ከሁለት  መስመር በላይ ያላቸውን መንገዶች እንዴት እንደምንሻር

አንዳንድ መንገዶች ሰፊ መንገድ ወይም ሶስትና አራት አሰፋልቶች አሏቸው፡፡

እያዳንዳቸውን በተናጥልና በጥንቃቄ  መመልከት፡፡

በዜብራ መሻገር

የዜብራ መሻገሪያ ካለ ምንግዜም በዛው እንሻገር፡፡

ከመሻገርዎ በፊት መንገድ ዳር ይቁሙ፡ መኪኖች መቆማቸውን ያረጋግጡ፡፡

 በሁለቱም በኩል መኪኖች መቆማቸውን ካረጋገጡ በኋላ በዜብራው ይሻገሩ፡፡

በጥንቃቄ መመልከትዎንና የሞተር ድምጽ ማዳመጥዎን አይዘንጉ ምክንያቱም እርስዎን ያላየ ሹፌር ሊኖር ስለሚችል፡፡

ማሳሰብያ፡- መሬቱ እርጥብ ከሆነ መኪኖች ለመቆም ጊዜ ይወስድባቸዋል

የውሀ ሙላትና የበረዶ ግግር ባለበት መንገድ እንዴት እንደምንሻገር

አብዛኛውን ጊዜ መኪኖች እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥም በአንድ መስመር ነው የሚሄዱት፡፡

የሚያልፉ መኪኖችን ይጠንቀቁ፡፡

መኪኖች ይቆማሉ ብለው እንዳያስቡ፡፡

ከመሻገርዎ በፊት መኪኖች እርስዎን ለማሻገር መቆማቸውን ያረጋግጡ፡፡

ትፊራክ ወይም ፖሊስ ያለበት የትምህርት ቤት መሻገርያ

በትምህርት ቤት አካባቢ ትራፊክ ባለበት ቦታ ትራፊኩ ተሻገሩ የሚል ምልክት እስከሚሰጣችሁ ቁሙ።

ትራፊክ የሚያዛችሁን ነገር አክብሩ፡ ስትሻገሩም በትራፊኩ ፊት ለፊት ተሻገሩ፡፡

በባለአንድ መስመር መንገድ መሻገር

መኪኖቹ በየትኛው አቅጣጫ እየሄዱ እንደሆነ ማረጋገጥ፡፡

ለመሻገር እርግጠኛ እስኪሆኑ ይጠብቁ፡፡

ብስኬሌት መንዳት

ብስክሌት በመንዳት ተዝናኑ ግን ሁልጊዜም እነዚህን ማሳሰብያዎች አስታውሱ

ዋናዎቹ፡-

ስልጠና ወስደው ካልሆነ በመኪና መንገድ ላይ ብስክሌት አይንዱ፡፡

ብስክሌት ለመንዳት ከመውጣታችሁ በፊት ከወላጆቻችሁ ወይም ከአዋቂዎች ጋር የትኛው መንገድ እንደሚሻል ተወያዩ፡፡

በብስክሌቱ በስተኋላና ከፊት በኩል አንጸባራቂዎች እንዳሉ ማረጋገጥ፡፡

አንጸባራቂዎቹን በንጽህና መያዝና ላያቸው ላይ ምንም ነገር አለመለጠፍ፡፡

እቃ መያዝ ከፈለጉ የብስክሌት ዕቃ ማስቀመጫ ማድረግ፡፡

ልብስዎ ካቴናና ጎማ ውስጥ የማይገባ ዓይነት ይሁን፡፡

የሚመች ጫማ ያድርጉ ነጠላ ጫማ አይሆንም፡፡

ከቁመታችሁ ጋር የሚስማማ ብስክሌት ይሁን ምክንያቱም በጣም ካነሰም ከተለቀም ሚዛኑን አይጠብቅም ስለዚህ አደገኛ ነው፡፡

ከመጀመራችሁ በፊት

ፍሬኖቹ በደንብ እንደሚሰሩ ማረጋገጥ ጎማዎቹም አለመተንፈሳቸውን ማየት፡፡

የአደጋ መከላከያ ኮፍያ አድርጉ አደጋ ቢያጋጥማችሁ ይከላከላል፡፡

ለዓይን የሚታይ ልብስ ልበሱ ምክንያቱም መኪና አሽከርካሪዎች እንዲያይዋችሁ፡፡

በጨለማ ብስክሌት መንዳት

በጨለማ ብስክሌት አለመንዳት ይመከራል፡፡

በጨለማ ከነዱ አንፀባሪቂ ወይም ፈካ ያለ ቀለም ልብስ ልበሱ፡፡

አንጸባራቂዎቹን ማጽዳት፡፡

በምትነዱ ጊዜ

ከመጀመራቹ ወደፊት ወደኋላ ተመልከቱ ብስክሌቱ በትክክል እንደሚሰራ ሞክሩት፡፡

የትራፊክ መብራቶችን አክብሩ፡፡

ምን ልታደርጉ እንደሆነ የሚያሳይ በቀላሉ የሚታወቅ የእጅ ምልክት ስጡ፡፡

ምልክት ለመስጠት ካልሆነ እጃችሁን ከመሪዎቹ ላይ አታንሱ፡፡

ስትጠመዘዙ ለእግረኞች ቅድሚያ ስጡ ምክንያቱም እግረኞች ከእናንተ ጋር በቀኝ በኩል ስለሚጓዙ፡፡

በምትነዱ ሰዓት ሌላ መኪና ወይም ብስክሌተኛ አትያዙ፡፡

ብስክሌት የመንዳት ልምድ ቢኖራችሁም ሌላ ሰው በብስክሌት ጭናችሁ አትሂዱ፡፡

የመኪና መጨናነቅ ባይኖርም ከሁለት በላይ ጎን ለጎን አትሂዱ ተከታትላችሁ ሂዱ፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ ባለበት መንገድ ወደቀኝ መጠምዘዝ ከፈለጋችሁ በግራ እጃችሁ በኩል ቁሙ ለመጠምዘዝ የምትችሉበት ክፍተት ስከሚፈጠር ጠብቁ፡፡

ብስክሌት በምትነዱ ሰዓት ሙዚቃ እየሰማችሁና ሞባይል ስልክ እያናገራችሁ አትንዱ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ሃሳባችሁን ይሰርቁታል፡፡

በቆሙ መኪኖች በኩል እየነዳችሁ ከሆነ ተጠንቀቁ ምክንያቱም ሊንቀሳቀሱ ወይም የመኪና በር ሊከፈት ይችላል፡፡

ላልተጠበቀ አደጋ ተዘጋጁ፡

ብስሌት ማቆም

ብስክሌታችሁን ስታቆሙ ለብስክሌቶች ተብሎ በተዘጋጀ ቦታ ላይ አቁሙ፡፡

ብስክሌታችሁን ቆልፋችሁ አስቀምጡ፡፡

የሚሻገሩ እግረኞች

እግረኞች በቀኝ መንገድ ስለሚሄዱ ምንግዜም በዜብራ እንዲሻገሩ አቁሙላቸው፡፡

በእንስሳቶች አጠገብ ብስክሌት መንዳት

ከእንስሳቶች ወይም ከጋሪዎች ራቅ ብላችሁ ንዱ

በመኪና መጓዝ

ምንግዜም ቀበቶ እሰሩ

በመስኮት መውጣት ወይም እጅን ማውለብለብ እቃ መጣል ወይም ማንጠልጠል አይቻልም፡፡

ሹፌሩ የሚያይበትን መስታወት አትከልሉ፡፡

ሹፌሩን  በማናገር ሀሳቡን አትስረቁት፣ መኪና ውስጥ አትጩሁ፣ አትጫወቱ ምክንያቱም ሹፌሩ ሀሳቡን ሰብስቦ ማሽከርከር አለበት፡፡

የመኪናውን በር ወይም መስኮት መክፈት ያለባችሁ ወላጆቻችሁ ሲያዝዋችሁ ብቻ ነው፡፡

በአውቶብስ መጓዝ

አውቶብስ በምትጠብቁበት ጊዜ በመንገድ ዳር ቁሙ በአውቶቢስ ማቆምያ ላይ እንዳትጫወቱ፡፡

ተራችሁን ጠብቁ ከመግባታችሁ በፊት የሚወርዱትን ጠብቁ ፡፡

ሌሎች ተሳፋሪዎችን አትግፋቸው፡፡

ከአውቶቢስ ከወረዳችሁ በኋላ የምትሻገሩ ከሆነ አውቶቢሱ ተነስቶ እስከሚሄድ ጠብቁ፡፡

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

Latest from Seyfu Mekonen