ደህንነት (safety)

Written by  Thursday, 22 October 2015 17:12
Rate this item
(0 votes)

ደህንነት (safety) ትርጉም

ደህንነት ማለት 

ስራን በተገቢ መልኩ መረዳት:

መወሰድ ያለበትን እያንዳንዱን እርምጃ ማወቅ፥

ስህተቶች ለራስና ለሚሰሩበት ድርጅት ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ፥

ደህንነት ማለት (safety means)

መልካም አስተውሎ፥ (good judgment)

እድል ላይ በፍፁም አለመመርኮዝ፥

ላልተጠበቁ ሁኔታዎች እራስን ማዘጋጀት፥

የተለመዱ ስራዎችን ሲያከናውኑ ንቁ መሆን፥

ደህንነትን መጠበቅ ማለት፥-

በርስዎ ስር የሚተዳደሩ ቤተሰብ፣ የሚሰሩበትን ድርጅትና ስራዎን ግምት ውስጥ ማስገባት፥

 

ከሚሰሩበት ድርጅት ውስጥ የሚወጡ የደህንነት መመሪያዎችን ሁሌ ማስታወስና መተግበር፥

ትርጉሞች

ከ 'After whiskey driving risky' ይህ ማለት ከጠጡ በኋላ መንዳት አደገኛ መሆኑን የሚያሳይ ከህንድ የተገኘ የመንገድ ማስጠንቀቂያ ቃል ነው፡፡

ደህንነትን በተመለከተ ሁለት ተቀራራቢ ትርጉሞች ይጠቀሳሉ፡፡ ለምሳሌ የቤት ውስጥ ደህንነት ማለት ህንፃው ከውጫዊ ጎጂ ነገሮች የአየር ሁኔታ፣ የቤት ዘረፋ ወዘተ የመከላከል አቅሙ ሊያመለክት ይችላል፡፡ በተመሳሳይ በቤት ውስጥ የተተከሉ መሳሪያዎች (በኤልክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የቤት እቃዎች፣ ደረጃዎች ወዘተ) ለቤቱ ነዋሪዎች አደገኛ አለመሆኑን ያመለክታል፡፡

ደህንነት መጠበቅ ስንል ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ ከነዚህ ሁኔታዎች አንዱ ጥበቃ (security) ሊሆን ይችላል፡፡ በጊዜ ሂደት የደህነትና የጥበቃ ትርጉም የሚመሳሰሉበት፣ የሚወራረሱበትና በአንድ አረፍተ ነገር ሁለቱም የሚጠቀሱበት ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ አለመታደል ሆኖ አምባቢዎች ቃላቶቹ በድግግሞሽ መፃፋቸውን ወይም አለመፃፋቸውን መረዳት የግድ ይላል፡፡ ይህ በራሱ እያንዳንዱ ቃል በትክክለኛ ሁኔታ መቀመጡንና አለመቀመጡን ግርታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በራሳቸው መንገድ ብቻ ሲታዩ  እያንዳንዱ ቃል ትክክለኛ ቦታውን እንዲይዝና አንዱ ባንዱ ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመረዳት ያግዛል፡፡

ደህንነትን መጠበቅ ማለት አንድ ድርጅት ወይም ቦታ በተቀመጠለት ሁኔታ ስራዎች ሳይዛነፉ መከናወናቸውን የሚያመለክት ሁኔታ ነው፡፡ ድርጅቱ የተቀመጡለት ስራዎች ማከናወን ማለት መንግስታዊ ህጎችና ደረጃዎች፣ ተያያዥ የአርክቴክቸርና የምህንድስና ዲዛይኖች፣ የኩባንያው ራእይና ተልእኮ፣ እና የተግባር እቅዶችና የሰራተኛ አስተዳዳር ፓሊሲዎች ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ ማንኛውም ትልቅ ወይም ትንሽ ድርጅት የቦታ ወይም የስራ ደህንነትን መጠበቅ ተገቢ ሃሳብ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ሁኔታ የሚጠበቅና ተቀባይነት ያለው ትርጉም እንደሚሰጥ ተደርጎ መቀመጥ አለበት፡፡

በዚህ ትርጉም መሰረት መኖሪያ ቤትን ከውጫዊ ስጋቶች መጠበቅ እና ከቤት ውስጥ እቃዎችና ቤቱ የተሰራበት ነገሮች (internal structure) መጠበቅ የተለያዩ የደህንነት ትርጉሞች ሳይሆን መኖሪያ ቤቱ በተቀመጠው መንገድ ደህንነቱ መጠበቁን የሚያመላክቱ ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡

በምናከናውናቸው እያንዳንዱ ስራዎች ሁሉም ነገር በታቀደለት መንገድ ላይጓዝ ይችላል፡፡ ያንዱ አካል የተቀመጠለት ትክክለኛ ሁኔታ ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙት ይችላሉ፡፡ የጥበቃ ሳይንስ (security science) እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት ባለፊት ጥቂት አመታት ተግባር ላይ መዋል የጀመረ ሳይንስ ነው፡፡

ከላይ የተሰጡን የደህንነት ትርጉሞችን መጠቀም፤ 

ጥበቃ (security) ማለት አንድን ድርጅት ከተቀመጠለት ትክክለኛ ሁኔታ ከሚያዘንፉና አላማውን እንዲያሳካ ከሚያደርጉት ውጫዊ ወይም ውስጣዊ ጉድለቶች፣ ጥፋቶች፣ ወንጀለኞች፣ ግለሰቦች ከሚያደርሱት ጉዳት ለመከላከል የምንጠቀምበት ሂደት ወይም ዘዴ ነው፡፡

ከላይ ከተቀመጠው የደህንነት አጠቃላይ ትርጉም በመነሳት የጥበቃ ፕሮግራም አካላትን በተገቢው ሁኔታ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

ውስኑነት (limitations) 

የደህንነት ጥበቃ አንድ ድርጅት ከሚያገኘው ዋስትና ወይም የኢንሹራንስ ደረጃና ጥራቱን የጠበቀ ስራ ጋር በተያያዘ ውስንነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ድርጅቱ መስራት ያለበትን ሰራ ብቻ እንዲያከናውን ለማረጋገጥ የምንጠቀምበት መሳሪያ ነው፡፡

የደህንነት ጥበቃ ስራ ተነፃፃሪ መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ሁሉንም አደጋዎች ለማስቀረት   በጣም አስቸጋሪና ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታ ማለት ጉዳቶችና በንብረት ላይ የሚያጋጥሙ ብልሽቶች ዝቅተኛና ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆኑ ማድረግ ማለት ነው፡፡

የደህንነት ጥበቃ አይነቶች (Type safety)

ተገቢውን ደረጃ በሚያሟሉ ደህንነታቸው በተጠበቀና ደህንነታቸው የተጠበቀ በሚመስሉ ምርቶች መካከል ያለውን ልዩነት መንገዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ የአውራ ጎዳና የደህንነት ጥበቃ ማህበረሰብ የሚጠቀምባቸው ፅንሰ ሃሳቦች እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡

ተገቢነት ያለው የደህንነት ጥበቃ (Normative safety)

ተገቢነት ያለው የደህነነት ጥበቃ አንድ ምርት ወይም ዲዛይን ተግባራዊ የሚሆኑ ደረጃዎችና ልምዶች ሲሟሉ የምናገኘው የደህንነት ጥበቃ አይነት ነው፡፡ ይህ የደህነነት ጥበቃ አይነት የምርቱን ያለፈ ታሪክ ግምት ውስጥ ላያስገባ ይችላል፡፡

ተግባራዊ የደህንነት ጥበቃ (preserved safely)

ይህ የደህንነት ጥበቃ አይነት ተግባራዊ የአለም የደህንነት ጥበቃ ታሪክ አመቺ ሲሆን ተግባር ላይ የሚውል ሲሆን ደረጃዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ሊተገበር ይችላል፡፡

ግለሰባዊ እይታ የደህነነት ጥበቃ (perceived safety)

ይህ የደህንነት ጥበቃ አይነት የተጠቃሚውን የምቾት ደረጃና የጉዳት እይታን የሚያመላክት ሆኖ ደረጃዎችንና የደህንነት ጥበቃ ታሪክን ግምት ውስጥ አላስገባም፡፡

ለምሳሌ የትራፊክ ምልክቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ መስሎ ሊታየን ይችላል፡፡ ነገር ግን ባንዳንድ መተላለፊያ ቦታዎች ላይ የትራፊክ ግጭቶች ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡ የመኪና መዞሪያ ደሴቶች ባጠቃላይ ደህንነታቸው የተጠበቀ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ አሽከርካሪዎች የመረበሽ ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡

ዝቅተኛ የደህንነት ጥበቃ እይታ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ለምሳሌ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር September 11/2001 የአሜሪካ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ አብዛኛው ሰው ከአውሮፕላን በላይ መኪና መንዳት ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ያስባል፡፡ ነገር ግን የሽብርተኞች ጥቃት ግምት ውስጥ ቢገባም በአውሮፕላን መብረር መኪና ከመንዳት በላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ግለሰባዊ የጉዳት እይታና ሁነታ  ሰዎች በእግር ከመጓዝና ሳይክል ለትራንስፖርትና ለመዝናናት ከመጠቀም ሲያደናቅፋቸው ተስተውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት በአካላዊ እንቅስቃሴ ከምናገኘው የጤና ጥቅም ይልቅ ሊደርስብን ለሚችለው ጉዳት ያመዘነ ግምት እንዲኖረን አድርጓል፡፡

ጥበቃ Security

ጥበቃ በተጨማሪ ማህበራዊ (social) ወይም ህዝባዊ (public) ደህንነት የሚባል ሲሆን ሆን ተብሎ በሚፈፀሙ የስርቆት የጥቃት የዘረፋ ወንጀሎች የሚከሰቱ ጉዳቶች ላይ ትኩረት ይሰጣል፡፡

ከዚሁ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በሚያከሰሩ የሞራል ጉዳዩች ምክንያት በአብዛኛው ሰዎች ጥበቃ (security) ከተግባራዊ የደህንነት ጥበቃ (substantive sfety) በላይ የላቀ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ለምሳሌ በአብዛኛው አገሮች የትራፊክ አደጋዎች የተለመዱ ቢሆኑም የግድያ ወንጀል ከትራፊክ አደጋ ይልቅ መጥፎ እንደሆነ ሰዎች ያስባሉ፡፡

ጉዳቶችና ግብረ መልሶች Risks and responses

የደህንነት ጥበቃ አጠቃላይ በሆነ መልኩ በጉዳት ምክንያት የሚከሰቱ ትክክለኛና የላቁ የሞት የጉዳት ወይም የንብረት መበላሸትን ሁኔታዎችን ያመለክታል፡፡ ለነዚህ የጉዳት እሳቤዎች የተለያዩ የምህንድስናና የቁጥጥር ግብረመልሶች እንደ መፍትሄ ሀሳቦች ሲቀርቡ ማየት የተለመደ አሰራር ነው፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ገጥሞናል ብለው ለሚያስቡት የደህንነት ዋስትናን (insurance) እንደ ግብረመልስ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አደጋ ወይም ጥፋት ባጋጠመ ጊዜ የገንዘብ ካሳ ስለሚያገኙበት ብቻ ነው፡፡

ስርአታዊ የደህንነት ጥበቃና አስተማማኝ ምህንድስና system safety and reliably enginering

ይህ ፅንስ ሀሳብ የምህንድስና አንዱ ዘርፍ ሆኖ ቀጣይ የቴክኖሎጂ ለውጦች፣ የአካባቢ ቁጥጥርና ህዝባዊ ደህንነት ጉዳዮች የደህንነት ጥበቃ ስርአትን በጥልቀት የመተንተን አስፈላጊነት በእጅጉ እንዲልቁ ግድ ይላል፡፡

እዚህ ላይ ለምሳሌ የሚቀርበው አደጋን በቀላሉ ማወቅ ይቻላል የሚለው የተሳሳት ግንዛቤ ይስተዋላል፡፡ በትክክለኛ ሁኔታ ግን የደህንነት ጥበቃ ጉዳዮች የብዙ መቶ አመታትና የሺዎች ባለሙያዎች ጥረት ታክሎበት አንድ በአንድ የታወቁ እንጂ፥ የአንድ የትምህርት ዘርፍ የተፃፉ ፅሁፎችንና የተለመዱ ደረጃዎችን ማወቅ ለደህነነት ምህንድስና እጅግ አስፈላጊ አካላት ናቸው፡፡ የፅንሰ ሀሳብና የአሰራር ልምዶችን ጥምር ግንዛቤ በዚሁ መስክ የሚታዩትን ለውጦች ለመገንዘብ ያግዛል፡፡ 

ለምሣሌ፡- በአሜሪካ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው የኤሌክትሪካል ምህንድስና ባለሙያዎች በዚሁ ዘርፍ ተወዳዳሪ መሆን ቢገባቸውም አብዛኛዎቹ የኤሌክትሪካል መሃንዲሶች የስራ ፍቃድ እንዲኖራቸው አይገደዱም፡፡

አብዛኛውን ጊዜ የደህንነት ጥበቃ ጥራት - አስተማማኝነት - አቅርቦት - ጥገናና ደህንነት የሞያ ዘርፎች አጠቃልሎ የሚይዝ ጉዳይ እንደሆነ ይሰማናል፡፡ (አንዳንዴ አቅርቦት አስተማማኝነትና ጥገና አንዱ አካል ተደርጎ ስለሚወሰድ ለብቻው ሲጠቀስ አይታይም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች የአንድ ስራ ተቀባይነት የሚወሰኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በአንዱ ላይ የሚከሰት እጥረት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ በዚህም ምክንያት መልካም አመራር ወጪን እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡፡

 

በአጠቃላይ ደህንነት ወይም ሴፍቲ የሚለው ቃል፡- ከአደጋ፣ ከጉዳት፣ ከስጋት ነፃ መሆን ማለት ሲሆን እንዲሁም የግል ጥበቃ ወይም ሴኩሪቲንም ያጠቃልላል፡፡ ደህንነት የሚለው ቃል ለብዙ ጊዜ ከመጠቃማችን የተነሳ አብዛኞቻችን ቃሉን ስንሰማ በአካሄዳችን ጥንቃቄ ለመውሰድ ወይም ጎጂ ልማዶችን ለመቀየር እንደ ማስጠንቀቂያ እንቆጥረዋለን፡፡

አሁን ግን ደህንነት የሚለውን ቃላት ሲሰሙ በህይወትዎ ውስጥ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ከጉዳት የሚጠብቅዎ አሰራር አድርገው ያስቡት፡፡

ለምሳሌ፡- በሰላም እያሽከረከሩ ከሆነ መኪናዎን ማሽከርከር ያለብዎት መንገድ ትክክለኛ  እንደሆነ ማረጋገጥና በዚህም ህጉንም እያከበሩ ነው ማለት ነው፡፡ የዓይን ጥንቃቄ በሚያስፈልገው ሥራ እየሰሩ ከሆነ ዝም ብለው አይስሩ የአይን መከላከያ መነጽር አደርገው ይስሩ፡፡ በቤትዎ ውስጥ እየሰሩ ከሆነ ወንበር ላይ ቆመው አይስሩ መሰላል ይጠቀሙ ምክንያቱም ወንበሮች የተሰሩት ለመቀመጫነት ብቻ ነው፡፡

ደህንነት ምን ማለት፡-

1.  ደህንነት ማለት የሚሰሩትን ስራ በትክክል መረዳትና እያንዳንዱ የሚያደርጉትን ነገር ማወቅ፡፡ እንዲሁም ስህተት ለእርስዎም ሆነ ለካምፓኒዎ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ማወቅ፡፡

2.  ደህንነት ማለት ጥሩ አመለካከት፣ በዕድል አለማመን፣ ያልተጠበቀ ነገር ቢያጋጥም ነገሩን ለመቆጣጠር  ዝግጁ ሆኖ መጠበቅና ስራዎን በሚሰሩ ሰዓት በንቃት መሰራት፡፡

3.  ደህንነት ማለት በእርስዎ ስር ላለ ቤተሰብዎ፣ ለሚሰሩበት ካምፓኒና ለራስዎ ደህንነት ማሰብ፡፡

4.  ደህንነት ማለት በሚሰሩበት ካምፓኒ የተሰሩትን ህጎች ማስታወስና በስራ ሰዓት ሁል ጊዜ መተግበር፡፡

 

አንድ ስህተት ሊያገግሙበት የማይችሉትን አደጋ ሊያስከትል ይችላልና፡፡

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety ደህንነት (safety)