ክራክ ኮኬይን ምንድነው?

Written by  Friday, 13 November 2015 01:56
Rate this item
(3 votes)

ክራክ ኮኬይን ምንድነው?

 

ኮኬይንና ክራክ በጣም አነቃቂ ንጥረ ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ንቃትና ሀይልን የሚጨምሩ አደንዛዥ እፆች ናቸው ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ኮኬይንና ክራክ ልክ እንደ ሁለት የተለያዩ አደንዛዝ እፅ ያደናግራሉ፡፡ እውነታው ግን ተመሳሳይ : አደንዛዥ ዕፅ  ግን የተለያዩ ናቸው፡፡

ኮኬይንና ክራክ የሚገኙት ከኮካ ቡሽ (coca bush) ሻይ ቅጠል የሚመስል በደቡብ አሜሪካ የሚበቅል አበረታች እፅ ተክል ነው፡፡

ኮኬይን ሽታ አልባ ነጭ ዱቄት ነው ክራክ ደግሞ ከኮኬይን ዱቄት ቤኬንግሶዳ (baking soda) እና ከአሞኒያ (Ammonia) ይሰራል፡፡

ኮኬይን በአፍ በማጨሰ በመርፌ በመውጋት በአፍንጫ በመሳብ ይወሰዳል፡፡ በአፍንጫ በማጨስ ወይም በመርፌ በመውጋት ሲወሰድ ከ 30 እስከ 40 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል፡፡ ክራክ ግን በአፍ የሚጨስ ሲሆን ከ 10 እስከ 15 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል፡፡

ኮኬይን በአጭር ጊዜ ሲወሰድ የሚያደርሰው ጉዳት እና የኮኬይን ተጠቃሚዎች የሚያሳዩት ምልክቶች፥

ኮኬይን እንደ አነቃቂ እፅ የሚጠቀም ሰው የሚከተሉት ነገሮች ይታይበታል፡፡

የአፍ መድረቅ፣ አይን መፍጠጥ

የደስታ ስሜት፣ የድፍረት ስሜት

የልብ ምት መጨመር፣ የደም ግፊት መጨመር፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ

ከፍተኛ የኮኬይን መጠን መውሰድ ጉዳቱ፥

የስጋት ስሜት ፣ የኃይለኝነት ባህሪ፣ የሌላ ድምፅ መስማት ፥ የሌለ ነገር ማየት፣ ራስምታት፣ የማየት ችግር፣ የደረት ህመም፣ ድንገተኛ የሰውነት መኮማተር በአንድ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ኮኬይን ከተወሰደ በስትሮክ (strook) ራስን በመሳት ህልፈተ ህይወት ያመጣል፡፡ የመተንፈስ ችግር ወይም ልብ ህመም ያመጣል፡፡

 

የኮኬይን የጎንዮሽ ጉዳቶች

ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን ለረዥም ጊዜ የሚወስድ ሰው ለሚከተሉት ነገሮች ይጋለጣል፡፡

የጎሮሮ ወይም የሳንባ መቆጣት

ራስ ምታት

ለስንፈተ ወሲብ በተለይ ለወንዶች

የማስታወስ ችግር፣ ትኩረት ማጣት ችግር

ክብደት መቀነስ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣

የጥርስ መበላሸት

የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ

የልብ ሕመም፣ እራስን መሳት (stroke)

የድብርት ስሜት ፣ ሀዘን ስሜት፣ ካለምክንያት የመፍራት ስሜት

መሰረት የሌላቸው ነገሮች በኃሳብ መስማትና ማየት።

የኮኬይን ተጠቃሚዎች በአፋቸው የሚያጨሱት በአፍንጫቸው ከሚስቡት የበለጠ በቀላሉ እና በፍጥነት  በሱሱ ይያዛሉ፡፡ ምክንያቱም ኮኬይን በአፍ ሲጨስ ከፍተኛ መጠን ያለው የኮኬይን ንጥረ ነገር በፍጥነት ወደ አንጎል ስለሚገባ ነው፡፡

አዘውትረው ክራክ እና ኮኬይን የተባሉትን አደንዛዥ እፆች የሚጠቀሙ ግለሰቦች በሱሶቹ አማካኝነት አካላዊና ሳይኮሎጂካዊ ጥገኝነት ያድርባቸዋል፡፡ ኮኬይንና ክራክ ሕገወጥ አደንዛዥ እፆች ሲሆኑ እነዚህን እፆች መያዝ፣ መጠቀም፣ ማምረት ወይም መሸጥ በሕግ ያስጠይቃል፡፡

በተጨማሪም እነዚህ አድንዛዥ እፆች በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ ከሆነ፡-

ህፃኑ ከመወለጃው ቀን በፊት ሊሞት ይችላል፡፡

ያለጊዜው ውልደት፣ ክብደቱን ቀንሶ ሊወለድ ይችላል፡፡

ከውልደት በፊት እራስን መሳት፣ አይምሮ ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል፡፡

ባጠቃላይ እነዚህን አደንዛዥ እጾች የሚወስዱ ሰዎች እራሳቸውን ከፍተኛ አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ፣ ለልቅ የግብረስጋ ግንኙነት በመዳረግ ለኤችአይቪና ለመሳሰሉት በሽታዎች ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Health and safety ክራክ ኮኬይን ምንድነው?