የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ መንገዶች

Written by  Monday, 27 April 2015 01:54
Rate this item
(3 votes)

 

የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ መንገዶች

 

ቅድሚያ መቆጣጠሪያዎች

 

የጭስ መቆጣጠሪያ

በጭስ መቆጣጠሪያዎች እሳት መነሳቱን በማመልከት የማምለጫ መንገድና ሰዓት ያመቻቻሉ፡፡

መቆጣጠሪያዎቹም በእያንዳንዱ የቤት ክፍሎች ውስጥ መኖር ይኖርባቸዋል፡፡

የተመረተበትን ድርጅት መመሪያ በመከተል ሙከራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የደከሙ ወይም ጨርሰው የጠፉ ባትሪዎችን መተካት ያስፈልጋል፡፡

የመብራት ኃይል በሚቋረጥበት ጊዜ የጭስ መቆጣጠሪያዎች እንደማይሰሩ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በተጨማሪ ትርፍ በባትሪ ብቻ የሚሰሩ መቆጣጠሪያዎችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡

 

ከእሳት አደጋ ማምለጫ መንገዶችን ማዘጋጀት

ከእሳት አደጋ ማምለጫ እቅድ በማዘጋጀትና በመለማመድ ሁሉም ሰው በአደጋ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለበት ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡

የተዘጋጀውን የማምለጫ እቅድ ከሁሉም የቤት አባላት ጋር መለማመድ

በመስኮትና በበር በኩል ሁለት ከቤት መውጫ መንገዶችን ማሰብ ከፍተኛ ጭስ በተከሰተ ጊዜ ንፁህ አየር ወደ መሬት ወለል እንደሚወርድ ማስተዋል

በእጅና በጉልበት መሬት በመያዝ ወደ ቀረበው መውጫ መጓዝ፡

ውጪ ላይ የመገናኛ ቦታ ማዘጋጅት እንዲሁም ለፓሊስ የመደወያ ሁኔታ ማመቻቸት፡

በምንም ሁኔታ ለምንም ሲባል ወደ ውስጥ አለመመለስ።

 

    {youtube}2nt0DT0nXq8{/youtube}

 

የምግብ ቤት ደህንነት አጠባበቅ

ምግብ በመስራት ሂደት ላይ ሆኖ በፍፁም ትቶ አለመውጣት፡

ልጆችን ከኤሌክትሪክ ምድጃ አካባቢ ቢያንስ አንድ ሜትር ያህል ማራቅ፡

በማብሰል ጊዚ ሰፊና ረዥም ልብሶችን ከመልበስ መቆጠብ እንዲሁም የጋሉ እቃዎችን ላለመንካት መጠንቀቅ፡

ድስት ወይም ሳህናችን እሳት ከያዘ፤ እሳቱን ለማጥፋት በመክደን ምድጃውን ማጥፋት፡

የሳህናችንን እጀታ ወደ ውስጥ አድርጎ ማኖር፡ ይህም ህጻናት በቀላሉ እንዳይጎትቱት ይረዳል።

 

የሻማ ደህንነት አጠባበቅ

በቤት ውስጥ እንስሳት ወይም ህፃናት አጠገብ ጨርሶ አለመጠቀም

ከመተኛት ወይም ከመውጣት በፊት ሻማዎችን ማጥፋት

ሻማዎችን በማስቀመጫቸው በማኖር ከሚነዱ ነገሮች ቢያንስ 1 ሜትር ወይም 1 ጫማ ርቀት ላይ ማድረግ

 

የአካባቢ ማሞቂያዎች

የአካባቢ ማሞቂያዎች ሰፊ ቦታ ያስፈልጋቸዋል

ተንቀሳቃሽ እና ቋሚ ማሞቂያዎችን ከሚነዱ ነገሮች ቢያንስ 1 ሜትር ማራቅ

ማሞቂያዎችን አብርቶ (በስራ ላይ) ትቶ አለመውጣት ወይም አለመተኛት፡

ህፃናትንም ከዚህ ማራቅ፡

 

የትንባሆ ጭስ

የሲጋራ ተጠቃሚዎችን ከቢት ውጪ እንዲጠቀሙ ማድረግ።

ወደ ውስጥ የሰረጎዱ የሲጋራ መተርኮሻዎችን ማዘጋጀት

አመዱን ከመድፋት በፊት ሙቀታቸው መልቀቁን ማረጋገጥ፡

በሶፋ ወይም በማንኛውም ወንበር ላይ በአልጋ ላይም ሊሆን ይችላል በእንቅልፍ ስሜት ሆኖ ማጨስ አደገኛ መሆኑን ማስተዋል፡

የሚያጨሱ ሰዎች ከመተኛታቸው በፊት ያጨሱበትን ቦታ የሚከታተልላቸው ሰው ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም በእንቅልፍ ስሚት እሳቱ ኣደጋ ሊያስከትል ስለሚችል።

 

ክብሪት እና ላይተሮች

ክብሪትና ላይተርን ከህፃናት ክልል ውጪ በከፍታ በተለይ በተቆለፉ ቦታዎች ማኖር።

መገልገያነታቸው ለአዋቂ ሰዎች ብቻ መሆኑን ለህፃናት ማስገንዘብ።

 

ኤሌክትሪክ

ማንኛውም በጥቅም ላይ ያለ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ጭስ ካሳየ ወይም የመቃጠል ሽታ የመሳሰሉትን ምልክት ካሳየ ቶሎ በማጥፋት ችግሩን መረዳት፡

የተበላሸ ወይም በመበላሸት ላይ ያለ የመሳሪያ ክፍል ካለ ከወዲሁ በሌላ መተካት፡

በኤሌክትሪክ እቃዎች ላይ ከአቅም በላይ እቃ አለመጫን፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችን በምንጣፍ ስር በፍጹም አለመዘርጋት፡

የፊውዝ ሳጥኖችን አለመነካካት፣ ተገቢ መጠን ያላቸው ፊውዞችን መጠቀም፡

የቡና መጭመቂያ፡የሻይ ማፍያ ወይም የዳቦ መጥበሻ አይነት መሳሪያዎችን ተጠቅመው ሲጨርሱ ማጥፋት፡

 

ልብሳችን በእሳት ቢያያዝ

ባሉበት ቦታ መቆም፡

ቀስ ብሎ መሬት ላይ መተኛት ፊትን በሁለት እጅ መሸፈን

እሳቱ እስኪጠፋልን ድረስ መንከባለል (ወደ ጎን መገለባበጥ)

 

የሀይል መቋረጥ 

ሀይል በሚቋረጥበት ጊዜ ቤት ውስጥ ነዳጆችን ወይም ከሰል መጠቀም አይመከርም፡

ቤት ውስጥ ጋዝ መጠቀም ተገቢ አይደለም፡

ተንቀሳቃሽ ጀነሬተሮችን መጠቀም ካስፈለገ በትክክል ካልተዘረጋ በስተቀር ከቤት እቃዎች አለመጠቀም፣ ከቤቱ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ጋር አለማገናኘት ያስፈልጋል

ጀነሬተሩ በውጪ መቀመጡንና ጭሱ ወደ ተገቢ ቦታ እየሄደ መሆኑን ማረገገጥ፡

አሁን የጭስ መቆጣጠሪያችንን መሞከር ያስፈልገናል፡ ሀይል ሲቋረጥ ስራ አቁሞ ከሆነ በተቀያሪ በባትሪ የሚሰሩ መቆጣጠሪዎችን ለተጨማሪ ጥንቃቄ መጠቀም ያስፈልጋል።

 

የጋራ መኖሪያዎችና የትልልቅ ህንፃዎች ደህንነት

የሚከተሉት መረጃዎች ለተለያየ የህንፃ አይነቶች የተዘጋጁ በመሆናቸው ለእርሶ ህንፃ የሚሆነውን መምረጥ ይጠበቅቦታል፡፡

 

በእሳት አደጋ ጊዜ መውሰድ ያለብን እርምጃዎች

በእሳት አደጋ ጊዜ ሊፍት ተጠቅሞ መንቀሳቀስ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም የሊፍቱ መቆጣጠሪያ በሙቀቱ ምክንያት ስራ አቁሞ አደጋው ቦታ ላይ ሊጥሎት ይችላል፡፡ ይህም ማለት በጭስ የታፈነና የሊፍቱ በሮች መዘጋት የሚችሉበት ቦታ ማለት ነው፡፡

እንዲሁም የእሳት አደጋ መከላከያ ስራተኞች የኤሌክትሪክ ሀይሉን ካጠፉት ሊፍት ውስጥ ተዘግቶ መቅረትን ያስከትላል፡፡ እነዚህ ሰራተኞች ለራሳቸውና ለዕቃ መጓጓዣ ሌላ ሊፍት ሊያስፈልጋቸው ወይም ሊጠቀሙ ይችላል፡፡

 

በቤት ወይም በመስሪያ ቤት እሳት አደጋ ቢነሳ ማድረግ ያለብን ተግባራት

በተቻለ መጠን ለሁሉም ሰው በፍጥነት መንገር፡

በፍጥነት መውጣት ከወጡ በኋላ በሮችን ሳይቆልፉ መዝጋት፡

የሚቻል ከሆነ የህንፃውን የእሳት አደጋ ድምፅ ማሰሚያውን በመጫን ማስጮህ፡

የእሳት አደጋ ብርጌድ በመደወል ተገቢውን መረጃ በሙሉ መስጠት (ከእሳቱ በርቀት ሆኖ)፣ ሌላ ሰው ደውሎ ይሆናል ብሎ በፍፁም አለመገመት፡ 

የመውጫ ደረጃዎችን መጠቀም፡

የተቻለውን የማምለጫ መንገድ መጠቀም፡

ደህንነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ወደ ህንፃው አለመመለስ፡

 

የእሳት አደጋ ጥሪ ሲሰማ

በተቻለ ፍጥነት መውጣት

ማንኛውንም በር ከመክፈት በፊት የበሩን መያዣ እንዲሁም የበሩን ስሜት መመልከት፣ ከታች ወደ ላይ ማጥናት ሙቀት ከሌለው ቀስ ብሎ መክፈት፡

ከውስጥ ጭስ ወይም የመቃጠል ስሜት ካለ ቶሎ መዝጋት፡

የውጪው ሁኔታ ነፃ ከሆነ በሮቹን ዘግቶ በደረጃዎቹ በመጠቀም መውረድ፡

ጭስ ያለበትን ቦታ ጎንበስ ብሎ ማለፍ፣ ጭሱ አላስኬድ ካለ ባለው የተሻለ ቦታ ላይ መቆየት፡

ውጪ ወጥተው ከሆነ ተገቢው ቦታ በመደወል አስፈላጊ መረጃ ማቀበል፡

ኣሁንም ሌላ ሰው ደውሎ ይሆናል ብሎ በፍጹም ከመደወል አለመቆጠብ፡

 

ከቤት መውጣት ካልቻሉ ወይም መመለስ ግድ ከሆነ

የቤቱን በሮች መዝጋት ግን አለመቆለፍ፡

ጭስ ሊገባባቸው የሚችሉበትን ቀዳዳዎች በሙሉ በፎጣና በተገኘው ጨርቅ መድፈን።

ወደተሻለው የቤቱ ክፍል መሄድ መስኮቶችን ለአየር ማስገቢያነት መክፈት ጭስ የሚያስገባ ከሆነ በፍጥነት መዝጋት።

 

መሬት ላይ አጎንብሶ መቆየት (ሙቀትና መርዛማ ጭስ ወደ ላይ ስለሚወጣ)

ፎጣ ወይም ነጭ ጨርቅ ወደውጪ በማውለብለብ የአደጋ ሰራተኞችን ለመጥራት መሞከር (ምልክት መስጠት)።

መረጋጋት፣ በትዕግስት መጠበቅ፣ በመስኮት ከመዝለል መቆጠብ፡

በህንፃው የድምፅ ማስተላለፍያ የሚሰማውን መረጃና ትዕዛዝ በትክክል ማዳመጥ።

 

የአረጋውያን ደህንነት

ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ይህ አደጋ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ከሌለው የእድሜ ክልል ይልቅ የመጎዳታቸው መጠን በእጥፍ ይጭምራል፡፡ ከ75 በላይ ለሆኑ መጠኑ 3 እጥፍ እንዲሁም ከ85 እድሜ በላይ ለሆኑ 4 እጥፍ ሊሆን ይችላል፡፡

አብዛኛው የእሳት አደጋ የሚከሰተው በቤት ውስጥ በመሆኑ አረጋውያን እንዴት መዳን እንደሚችሉ ማስገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

በተወሰኑ የጥንቃቄ ደረጃዎች አረጋውያን ከሞት ወይም ከማንኛውም ጉዳት ሊድኑ ይችላሉ

 

ህይወትዎን አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ ያጭሱ

በሚመች ወንበር ላይ ዘና ብሎ ተቀምጦ ሲጋራ ማጨስን መዝናኛ የሚያደርጉ ሊኖሩ ይችላል፡፡ ነገር ግን መገንዘብ ያለብን ሲጋራና ዘና ብሎ መቀመጥ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ነው፡፡ እያጨሱ በእንቅልፍ መወሰድ ልብስን፣ ምንጣፍን ወይም የተቀመጥንበት ሶፋ በእሳት ሊያያዝብን ይችላል፡፡ በተጨማሪም የአልኮል መጠጦችን ወይም መድሀኒቶችን መጠቀም ነገሩን በይበልጥ ያባብሱታል፡፡

ጥንቃቄ የጎደለው የሲጋራ አጠቃቀም የመጀመሪያ ደረጃ በእሳት አደጋ ለሚከሰት ሞት እና ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ነው፡፡ እንዲሁም ከ65 ዓመት እድሜ በላይ ለሚሆኑ ግንባር ቀደም መሪ የጉዳት መንስኤ ነው፡፡ ሲጋራ በትክክል ካልጠፋ አንደገና የመቀጣጠል ሀይል አለው ምክንያቱም ሙቀት ለረጅም ጊዜ አብሮት ይቆያልና፡፡

 

ሲጋራ ከመለኮስ በፊት ማስታወስ የሚገባን

ተኝቶ አለማጨስ፡

የእንቅልፍ ስሜት ሲሰማ በደንብ ማጥፋት፡

በደንብ የሰረጎዱ መተርኮሻዎችን መጠቀም፡

በደንብ ያልጠፋ ሲጋራ ትቶ አለመሄድ፡

ህፃናት በቤት ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ክብሪቱን ወይም ላይተሩን ማራቅ ከተቻለ መቆለፍ፡

 

በማብሰል ሂደት ላይ

ብዙ ቤተሰቦች አንድ ላይ በመአድ ቤት ውስጥ ጊዜ ማሳለፍ ያዘወትራሉ። ተገቢ የማብሰል ሂደት ከሌለ ግን ከአደጋ መከሰቻ ቦታዎች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ የማብሰል ሂደት ከአደጋ መከሰቻ መንገዶች ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ይመራል። 

በማብሰል ሂደት ላይ ረዥም ልብስ መልበስ፣ ምድጃውን ስራ ላይ እንዳለ ትቶ መውጣት ወይም ተቀጣጣይ እቃዎችን በቅርብ (ምድጃው አካባቢ) ማስቀመጥ ለሞትና ለከፍተኛ አደጋ እንደሚያጋልጡ ግልፅ ነው፡፡

 

የቤተሰብ እራት ወይም የህፃናት ምግብ በሚዘጋጅበት ጊዜ

የማብሰያውን ቦታ ትቶ አለመሄድ ምክንያቱም በሰከንዶች ውስጥ እሳት ወደ ሌላ ቦታ ሊቀጣጠል ይችላል፡፡

ቀለል ያሉና ከሰውነት ጋር የሚያያዙ ልብሶችን መልበስ እንዲሁም ማንኛውም አይነት የመጠቀሚያ ጨርቆችን ከምድጃው ማራቅ ይገባል፡

ምድጃውን በፍፁም ለቤት ማሞቂያነት አለመጠቀም።

ወደ እንቅልፍ ከመሄድ በፊት ወይም ወደውጪ ከመውጣት በፊት የመዐድ ቤቱን ሁኔታ ደጋግሞ መፈተሸ ያስፈልጋል።

 

የቤት ማሞቂያ

በክረምት ወራት ከሌላው ጊዜ በተለየ የቤት ማሞቂያ እሳቶች ይለኮሳል፡፡ የማሞቂያ መሳሪያዎች የእንጨት ምድጃዎች ቤታችንን ምቹ ያደርጉልናል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ሙቀት በእሳት አደጋ ከሚከሰት የሞት ወይም ተያያዥ አደጋዎች ሁለተኛ ደረጃ መሪ ምክንያት ነው፡፡ እንዲሁም እድሜያቸው ከ65 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሶስተኛ ደረጃ አደጋ ፊጣሪ ነው፡፡

አብዛኛው ጉዳት ሙቀትን በመቆጣጠር ማስቀረት ይቻላል፡፡ የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ሀሳባችንን ለማሟላት ይረዳናል፡፡

በቤት ውስጥ የምንጠቀምበትን እሳት በተገቢው ሁኔታ ይዞ የሚያስቀር የተመቻቸ ቦታ ማዘጋጀት፡፡

የአየር ማሞቂያዎች ሰፊ ቦታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንዲሁም ተቀጣጣይ ነገሮች ከማሞቂያው ቢያንስ አንድ ሜትር ማራቅ ተገቢ ነው፡፡

ማሞቂያውን በምንገዛበት ጊዜ ምንም አይነት ችግር ቢፈጠር እራሱን ማጥፋት እደሚችል ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

 

በአደጋ ጊዜ ከቤት በሰላም ለመውጣት

የጭስ መቆጣጠሪያ

መቆጣጠሪያዎችን በየቤቱ በማኖር ድምፅ  እንደሚያስማ ማረጋገጥ፡

በአመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ የማምለጫ እቅዶችን ማዘጋጀት፡፡ ምን ማድረግ እና ወደ የት መሄድ እንዳለብን ጠንቅቆ ማወቅ፡፡

 

በጭስ ማምለጫ መንገድ

እብዛኛው ጉዳት በጭስ እንጂ በእሳት የተነሳ አይደለም፡፡ ጭስ በተነሳ ጊዜ ከመሬት ቅርብ መሆን ይጠበቅብናል፡፡ በእጅና በጉልበት መሬት በመያዝ ወደሚቀርበው መውጫ መሄድ ያስፈልጋል፡፡

 

በቤት ውስጥ መዘጋጋት ከተፈጠረ

በሮችን መዝጋት ግን አለመቆለፍ ለእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ሰራተኞች አመቺ ሁኔታ መፍጠር

እርጥብ ፎጣ ወይም ጨርቅ በመጠቀም ጭስ ሊገባባቸው የሚችልባቸውን ቀዳዳዎች በሙሉ መድፈን

ከተቻለ መስኮቶችን በመጠኑ መክፈት ጭስ የሚገባበት አጋጣሚ ካለ ግን መዝጋት፡

መሬት ላይ ተኝቶ መቆየት፡

በፎጣ ወይም ማንኛውም ጨርቅ አደጋ ጊዜ ሰራተኞች ምልክት መስጠት፡

ተገቢው ቦታ በመደወል በቂ መረጃ ማቀበል፡

እራስን ማረጋጋት፡

እንዴት መውጣት እንደሚቻል የሚነገር ካለ በፅሞና ማዳመጥ፡

Last modified on Monday, 27 April 2015 03:40
Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home Safety Fire safety የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ መንገዶች