ካንሰር

Written by  Friday, 01 December 2017 01:39
Rate this item
(0 votes)

ሊያዘናጉን የማይገቡ 10 የካንሰር ምልክቶች

ብዙ ሃኪሞች ለካንሰር ህመም መጋለጥን ለሚያሳዩ ምልክቶች ትኩረት እንድናደርግ ሁሌም ይመክራሉ። በካንሰር ሙሉ በሙሉ ከመጠቃታችን አስቀድሞ ዶክተሮች ከደረሱበት ህመሙን መፈወስ ይቻላል። 

ከዚህ በታች የምንመለከታቸው ነጥቦችን በፍፁም ቸል ልናላቸው እንደማይገባ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። በአለማችን ከ200 በላይ የካንሰር አይነቶች የሚገኙ ሲሆን፥ የተለመዱት የሳንባ፣ የጡት፣ የኩላሊት፣ የጉበት እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው።

ቀጥሎ አስሩን የካንሰር የማስጠንቀቂያ ደወሎችን የዘረዘርንላችሁ ሲሆን ሁሉም ሰው ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ ሁላችንም አሁኑኑ ሼር እንድናደርገው ሳይቴክ ይጠይቃል።

1.  ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ

ብዙ ጊዜ ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ ዋነኛው የካንሰር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። 

ከ40 በመቶ በላይ የካንሰር ተጠቂዎች ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ ተጋላጭ እንደሆኑ የሚነገር ሲሆን፥ በተለይም በሳንባና ጡት ካንሰር የተጠቁ ሰዎች ላይ ይታያል።

የክብደት መቀነስ የሚከሰተው ካንሰር ወደ ጉበታችን ሲስፋፋና የጉበትን ተግባር ሲያውክ ነው።

ስለሆነም ክብደት ለመቀነስ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እያደረግን ካልሆነና ሆን ብለን ምግብ ካልቀነስን በስተቀር ተከታታይ የክብደት መቀነስ የካንሰር ህመም ምልክት ሊሆን እንደሚችል ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

2.  ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖችና ትኩሳት

ትኩሳት ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ሰውነታችን ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚያደርገውን ትግል ተከትሎ የሚከሰት ቢሆንም ለረዥም ጊዜ የቆየ ትኩሳት የካንሰር ምልክት ሳይሆን እንደማይቀር ይነገራል።

የደም ካንሰርም ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች፣ ትኩሳት፣ ድካም እና የመሳሳሉ ምልክቶችን ያሳያል።

3.  ድካም እና አቅም ማጣት

ከፍተኛ ድካምና የአቅም ማጣት በእንቅልፍና እረፍት የማይሻሻል ከሆነ ሀኪሞችን ማማከር ያስፈልጋል።

ይህ የድካም ስሜት ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል።

4. የትንፋሽ መቆራረጥ

ትንፋሽ ማጠር በተለያዩ አጋጥሚዎች የሚከሰት ቢሆንም የሳንባ ካንሰር ምልክት ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል።

በተለይም አየር ወደ ወጪ በምናስወጣበት ወቅት የፊሽካ ድምፅ የሚመስል ድምፅ የምናሰማ ከሆነ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት ማምራት ተገቢ ነው ብለዋል ባለሙያዎቹ።

5. የማያቋርጥ ሳልና የደረት ህመም

ደረቅ ሳልና የጉሮሮ ቁስል የሳንባና ደም ካንሰር (ሉኪሚያ) ታማሚዎች ላይ በተደጋጋሚ ይከሰታሉ። ከዚህም በተጨማሪ ደረትን ሰቅዞ የመያዝ ስሜት ይሰማቸዋል።

ስለሆነም ተደጋጋሚ ደረቅ ሳልና የደረት ህመም ካስተዋሉ ሀኪሞን ያማክሩ።

ለስድስት ሳምንታት ያህል ከተለመደው ሁኔታ በተለየ የድምፅ መጎርነን በተለይም  በሚያጨሱ ሰዎች ላይ ከተከሰተ የሳንባ፣ የጉሮሮ እና መሰል ካንሰሮች መጋለጥን ሊያመላክት ይችላል።

6. የሆድ መነፋት

ያልተጠበቀና ሄድ መጣ የሚል የሆድ መነፋት ወይም መወጠር የካንሰር ምልክት ሳይሆን እንደማይቀር ነው የሚነገረው።

ከምግብ በኋላ ሆድ የመነፋትና የህመም ስሜትም የሆድ ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል። 

7.  ቃር

ቃር በሆድ ውስጥ የሚገኙ አሲዶች ወደ ጉሮሮአችን በሚመጡበት ጊዜ የሚከሰት የህመም ስሜት ሲሆን፥ ብዙ ጊዜ የተለመደ ነው።

ይሁን እንጂ ሁኔታው እየተደጋገመ ሲመጣ የጉሮሮ ካንሰር ምልክት ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች አረጋግጠዋል።

8.  የአንጀት ህመም

ያለምንም ምክንያት ለአራት ሳምንታት እና ከዚያም በላይ የዘለቀ የአንጀት ህመም በተለይም በአዋቂዎች ላይ ሲከሰት የአንጀት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።

9. ምግብ የመዋጥ ችግር

ምግብ የመዋጥ ችግር ወይም ምግብ በጉሮሮና በደረት ላይ ተጣብቆ የቀረ የሚመስል ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከሄደ የጉሮሮ ወይም የሳንባ ካንሰር ምልክት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

ትኩስ ምግቦችን ለመውሰድ ያለመቻል እና ይህን ተከትሎ የሚመጡ የህመም ስሜቶችም ከላይ የጠቀስናቸው የካንሰር አይነቶች ምልክቶች መሆናቸው ተነግሯል።

ምግብ የመዋጥ ችግር የሳንባ ካንሰር ምልክትም ሊሆን እንደሚችል ነው የሚነገረው።

10. የቆዳና አይን ቀለም መቀየር

የቆዳ ቀለም ወደ ቢጫነት እንዲሁም የአይን ቀለም ነጭነት መቀየር ብዙ ጊዜ የጉበት እና የሀሞት ጠጠር ህመሞች ምልክቶች ሲሆኑ፥ በተመሳሳይ ለጉበትና የጣፊያ ካንሰር ምልክቶችም ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገልጿል። 

ይሀ ዕሁፍ የተገኘው ከፊስቡክ ንወ>>

Seyfu Mekonen

Seyfu Mekonen is a founder and administrator of ethiosafety.com. As a founder and administrator he is responsible for free and up to date safety and security informations. He can be reached: seyfu2002@yahoo.com

You are here: Home